Translation is not possible.

ኡስታዝ አህመድ አደም

-------------

በሰው ስራ ትልቅ ሰው አይኮንም

በዘመናችን ሰርቶ መክበር ያቃታቸው፣ ስንፍና የተቆጣጠራቸው፣ አካላቸው ትልቅ አዕምሯቸው ትንሽ የሆነ፣ ከመተኛትና ከመብላት ውጪ ምንም ሳይሰሩ ኸይርም ይሁን ሸር ሰርተው ዕውቅና ካተረፉ ሰዎች ጎን በመቆም ታዋቂነትና ትልቅነት ለማግኘት የሚጥሩ ሰዎች በዝተዋል። ትልቅ ከሚሏቸው ሰዎች ጋ አብሮ ለመታየትና ፎቶ ለመነሳት ራሳቸውን ስተው ይሮጣሉ (ይቀብጣሉ)። ወንድሜ እውነተኛ ትልቅነት የሚገኘው በስራ ነው። ዋናው ነገር የአኺራህ ትልቅነት ነው። ይህ ደግሞ አላህን በመፍራት፣ በመልካም ስነምግባርና በበጎ ስራ ነው የሚገኘው!! ጊዜን በማይጠቅም ነገር ማጥፋትና እንደ ሕጻን እቃቃ መጫወቱን ትተን ፡ ያዘዘንን በመታዘዝ፣ የከለከለንን በመከልከል፣ የነገረንን አምኖ በመቀበል፣ በውሳኔው በመደሰት ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት እናሳምር። ለማይቀረው ጉዞም ስንቅ እናዘጋጅ። የተፈጠርነው ለጫወታና ለመዝናናት እንዳልሆነም አውቀን ለሞት እንዘጋጅ። በሁለቱም ዓለም ትልቅነት፣ ደስታና ስኬት የሚገኘውም በዚህ ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group