Translation is not possible.

እስራኤል ኤርዶጋንን አወገዘች !

እስራኤል በውጭጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ዛሬ ባወጣቺው መግለጫ የኤርዶጋን መግለጫ በጣም የሚያበሳጭ ነው ብላለች ።

" ሀማስ ከአይኤስ አይኤስ የባሰ አሸባሪ ሆኖ ሳለ ህፃናትና ሴቶችን የሚገድል ንፁሀንን አፍኖ የሚወስድ ህዝብን መመሸጊያ የሚያደርግ አሸባሪ ሆኖ ሳለ ኤርዶጋን ቡድኑን የነፃነት ታጋይ ማለታቸው እስራኤልን አበሳጭቷል እስራኤል ይሆንን የኤርዶጋን መግለጫ ታወግዘዋለች " ብላለች ።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በሰጡት መግለጫ ሀማስን የነፃነት አርበኛ ማለታቸው ይታወቃል ። እስራኤልንም ንፁሀንን ኢላማ ያደረገ የሽብር አገዛዝ ብለዋታል ።

ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ዛሬ አክለው በሰጡት መግለጫም ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት አታሻሽልም ብለዋል ።

ቱርክ ግዙፍ አውሮፕላኗ ለፍልስጤማውያን የእርዳታ ቁሳቁስ ጭኖ ወደ ግብፅ እንዲበር አድርጋለች ። በፖለቲካው ዘርፍም ኤርዶጋን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ሲሆን በፍልስጤም ጉዳይ ሙስሊም ሀገራትን ለማስተባበር እየጣሩ ይገኛሉ ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group