1 year Translate
Translation is not possible.

የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወደ እስራኤል ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰረዙ

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን እስራኤልን ለመጎብኘት የያዙትን እቅድ በዛሬው እለት መሰረዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን ለዚህም ምክንያታቸው በጋዛ ከሚገኙት የሃማስ ታጣቂዎች ጋር እስራኤል ባደረገችው “ኢሰብአዊ” ጦርነት ነው ብለዋል።

ኤርዶጋን ለገዥው ፓርቲ የህግ አውጭዎች በፓርላማ በሰጡት መግለጫ “ወደ እስራኤል የምንሄድበት ፕሮጀክት ነበረን፤ ነገር ግን ተሰርዟል፣ አንሄድም” በማለት ሃማስን ለገዛ መሬታቸው የሚታገል “ነጻ አውጪ” አድርገው ገልፀዋል።የኳታር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከቱርክ አቻቸው ጋር በዶሃ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በጋዛ የተገደሉት ህፃናት ቁጥር በዩክሬን ከተገደሉት ህፃናት ቁጥር ቢበልጥም "ተመሳሳይ ምላሽ አላየንም" ብለዋል። የኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ "የፍልስጤም ህጻናት ህይወት የማይቆጠር ይመስል ፊት የሌላቸው ወይም ስም የሌላቸው ይመስል"  የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ዘንግቷቸዋል ሲሉ ወቅሰዋል።

በሌላ በኩል በጋዛ ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች ወይም ከ35 ሆስፒታሉሽ 12ቱ መዘጋታቸው ተሰምቷል። በተመሳሳይ ወደ ሁለት ሦስተኛ የሚጠጉ የጤና አጠባበቅ ክሊኒኮች ወይም ከ72 የጋዛ ክሊኒኮች 46ቱ በጥቃት ወይም በነዳጅ እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቋል ።

በነዳጅ እጥረት ምክንያት የሆስፒታል የኃይል አማራጮች በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ሥራቸውን ያቆማሉ ሲል የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስጠንቅቋል። የእስራኤል “ጠቅላላ እገዳ” በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የህይወት አድን ስራ እያደናቀፈ ይገኛል።

በጋዛ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች መያዝ ከሚችሉት ሰው በአራት እጥፍ የበለጠ እያስጠጉ መሆኑ ተሰምቷል።በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከል በፈረቃ እንደሚተኙ ገልፀዋል።

በበረከት ሞገስ

#ዳጉ_ጆርናል #palestine #غزة #فلسطين #freepalestine #غزة_تحت_القصف #غزة_الآن #فلسطين_حرة #gazaunderattack #عاجل #palastine #الحرية_لفلسطين #gaza_under_attack #сионисты #израиль #minbarsveta1 #новости

Send as a message
Share on my page
Share in the group