Translation is not possible.

የሄዝቦላ መሪ ከፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች አመራሮች ጋር ድል በማድረግ ጉዳይ መከረ

October 25, 2023

የጦር መርከቦቿን ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ያስጠጋችውን አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት ደግሞ ከእስራኤል ጎን ተሰልፈዋል

የሊባኖሱ የሄዝቦላ መሪ ከፍልስጤም ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተገናኝቶ "ድል በማድረግ" ጉዳይ ተወያይቷል።

መሪው ከፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች ጋር መገናኘቱን ሮይተርስ የሄዝባላውን አል-ማናር ቴሌቪዥን ጠቅሶ ዘግቧል።

የአሜሪካ እና ኢራን የቃላት ጦርነት በተመድ

ተኩስ ይቁም ወይስ ጋብ ይበል?- የሩሲያ እና አሜሪካ ክርክር

እንደዘገባው ከሆነ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖቹ ሀማስ እና እስላማዊ ጅሃድ ከሄዝቦላ መሪ ጋር በተገናኙበት ወቅት በጋዛ ያለውን ትግል በድል ለማጠናቀቅ ጥምረታቸው ምን መሆን እንዳለበት ተወያይተዋል።

ስብሰባውን የሄዝቦላው ሰይድ ሀሰን ነስረላህ፣ የሀማስ ምክትል ኃላፊ ሳላህ አል አሮሪ እና የእስላማዊ ጅሃድ ኃላፊ ዛይድ አል ናቅሃላ ማካሄዳቸውን አል ማናር በዘገባው ገልጿል።

"በስብሰባው...በአለም አቀፍ ደረጃ የተያዘውን አቋም በመገምገም፣ ትግሉ ምን መምሰል አለበት" በሚለው ጉዳይ ምክክር መደረጉን ይኸው ሚዲያ ዘግቧል።

በሊባኖስ፣ ሶሪያ እና በየመን ያሉ ታጣቂዎች እንዲሁም ኢራን ከእስራኤል ጋር ለገጠመው ሀማስ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በሰሜን እስራኤል በኩል ጥቃት በመክፈት ለሀማስ ያለውን አጋርነት በተግባር በማሳየት ግንባር ቀደም ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት እስራኤል በዌስት ባንክ፣ በጋዛ እና በሰሜን እስራኤል በኩል እየተዋጋች ትገኛለች።

ሀሉት ግዙፍ የጦር መርከቦቿን ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ያስጠጋችውን አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት ደግሞ ከእስራኤል ጎን ተሰልፈዋል።

ሩሲያ እና የአረብ ሀገራት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢወተውቱም፣ እነአሜሪካ ትኩረታቸውን ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ ላይ ብቻ አተኩረዋል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group