Qumuqta qilghuchi yo'q.

እውነትን የተናገረ ዓለም አቀፍ ጀግና

--------

ይህ ሰው አምና "የአውሮጳ ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋች" ተብሎ የተመረጠው ከሪም ቤንዜማ ነው። ቤንዜማ ባለፈው ሳምንት "ሐማስን እንመታለን በሚል በፍልስጥኤማዊያን ላይ የሚካሄደው ገደብ የለሽ ጭፍጨፋ ይቁም! ለችግሮች ሰላማዊ መፍትሔ ይፈለግ" ብሎ በመናገሩ ብቻ የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር "አክራሪ ጽንፈኛ! የሙስሊም ብራዘርሁድ ዓላማ አቀንቃኝ! በቅርቡ ዜግነትህን ትነጠቃለህ" የሚል ውሳኔ ተላልፎበታል።

------

ዓለማችን በቀኝ አክራሪዎች ቁጥጥር ስር እየዋለች ነው። እስከ ዛሬ ድረስ ከተካሄዱት ጦርነቶች እና ፍጅቶች መካከል ብዙዎቹ የተለኮሱት በቀኝ አክራሪዎች ነው። ቀኝ አክራሪዎች በሀገር ውስጥ ተቃውሞን በሃይል የማፈን ስትራቴጂ፣ በውጪ ፖለሲ ደግሞ ለከት የለሽ የኢምፔሪያሊዝም የቁጥጥር መንገድ ነው የሚከተሉት። ዲሞክራሲ ለእነርሱ የማስመያ ስልት ነው። ሌሎች እነርሱን ካልመሰሉ ያጠፏቸዋል።

----

ቤንዜማን የገጠመው ችግር ብዙም አሳሳቢ አይደለም። ዜግነቱን ቢነጠቅ የሌላ ሀገር ዜጋ መሆን ይችላልና። ቀኝ አክራሪነት ግን ከምድረ-ገጽ መጥፋት ያለበት አስፈሪ አባዜ ነው። ይህ አባዜ በቶሎ ካልጠፋ ሌላ የናዚ የጥፋት ፍልስፍና አቀንቃኝ ሊወለድ ይችላል።

አላህ እነዚህን ጉልበተኞች እና ሸይጣን አምላኪዎች ጠራርጎ ያጥፋቸው አቦ!!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group