Translation is not possible.

ሂጅራ ባንክ ከኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ ኡለሞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል!

...

ሀሩን ሚዲያ ፦ጥቅምት 14/2016

...

ሂጅራ ባንክ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካቢቢዎች ለተውጣጡ ከ50 በላይ ኡለማዎች በኢስላማዊ የፋይናንሺያልና ተግዳሮቶች ፅንሰ -ሃሳቦች በተለይም በኢስላሚክ ባንክ አተገባበር ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የሁለት ቀናት የስልጠና መርሀግብ በአምባሰደር ሆተል እያካሄደ ይገኛል።

...

ስልጠናውን የሚሰጡት በኳታር ዩኒቨርስቲ የኢስላማዊ ህግና ዘመናዊ ጉዳዮች ፕሮፌሰር፣ በአለም የእስልምና ሊቃውንት ምክር ቤት የምርምር እና ፈትዋ ክፍል ሃላፊ፣ የዘመን ተኮር የእስልምና ህግጋት ፕሮጀክት መስራች፣ የኢስላማዊ ባንኮች ደረጃ መዳቢ ዓለም አቀፍ ድርጅት ቋሚ አባል እና በአሁን ሰዓት የሂጅራ ባንክ የበላይ አማካሪ በመሆን ስራ በጀመሩት ፕሮፌሰር ዶ/ር ፈድል ሙራድ ናቸው።

...

በዚህ የ2 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ50 በላይ ኡለሞች የሚሳተፉበት ሲሆን የስልጠናው የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ሼህ ሱልጣን አማን፣የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ጀማል ሙሳ፣የኦሮሚያ ኡለሞች ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል ገለቱ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የሒጅራ ባንክ አመራሮች ተገኝተዋል።

...

ይህ ስልጠና በሌሎችም የኢትዮጵያ ክልሎች እንደሚቀጥል ተገልጿል።

...

©ሀሩን ሚዲያ

image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group