Translation is not possible.

《8ቱ ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች》

🔸1/ ሆን ብሎ ከሰላት ጋር ግንኙነት የሌለውን ንግግር መናገር ሁለት ፊደል እንኳ ቢሆን

🔹2/ጠሃራና ውዱዕን የሚያፈርስ ነገር መከሰት

🔸3/መሳቅ

🔹4/ሰላት ሲሰገድ መሸፈን ያለበት የሰውነት አካል መገለጥ 📌(እዚህ ጋር ☞ልብ መባል ያለበት ነገር  ብዙ ሱሪና ሸሚዝ ወዘተ መሰል ነገሮችን ለብሰው የሚሰግዱ ሰዎች ጥንቃቄ ካላደረጉና ቲሸርት (ሸሚዛቸውን) ከሱሪያቸው  ወይም ከሽርጣቸው ስር በደንብ አስገብተው ቀበቷቸውን አጥብቀው ካላሰሩ ሱጁድና ሩኩዕ ሲያደርጉ ወገባቸው ከታች ይገለጣል በዚህም ሰላታቸው ይበላሻል!)

🔹5/ቂብላን ለቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ኋላ መዞር እንዲሁም ወደ ቀኝና ግራ አብዛኛውን የሰውነት አካል በጣም ማዞር

🔸6/ መብላት

🔹7/ መጠጣት

🔸8/ሰላት ውስጥ ሆኖ ሰላት ከሚሰግድ ሰው የማይጠበቅን ነገር በተከታታይ እየፈጸሙ መጫወት፡፡

🔘ማሳሰቢያ፦

1/ እነዚህን ነገሮች ረስቶ ወይም ባለማወቅ ወይም ሌላ ሰው በቁም ነገር አስፈራርቶና  አስገድዶት ከሆነ ያደረገው ሰላቱ አይበላሽም!

2/ ሴት ልጅ እየሰገደች:ـክንዷ ወይም እግሯ ወይም አንገቷና ትንሸም ቢሆን ፀጉሯ የታየና የተገለጠ እንደሆነ ሰላቷ ይበላሻል

🔸የምትሰግደው አጅነቢይ ያለበት ቦታ ላይ ከሆነም ፊቷንም ሙሉ መሸፈን ይጠበቅባታል።

ወላሁ አዕለም

✍ ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

     

Send as a message
Share on my page
Share in the group