Translation is not possible.

ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም

~

ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አጋሪዎችን በገንዘቦቻችሁ፣ በነፍሶቻችሁ እና በምላሶቻችሁ ታገሉ" ይላሉ። ነሳኢይ፣ አቡ ዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።

እውነት የሙስሊሞች ህመም ያምሃል? እንግዲያው ከሰሞንኛ ዋይታ ይልቅ ውሃ የሚያነሳ አስተዋፅኦ እንዲኖርህ ስራ። አላህ በሰጠህ ገንዘብ (ቢያንስ እንኳ) ብዙ ቁም ነገር መስራት ትችላለህ። ባቅራቢያህ ላሉ ሙስሊሞች ምን አድርገሃል? ዲንህን በማስፋፋት ላይ ምን ድርሻ አለህ? በምላስህና በብእርህስ ከእምነትህ ለመከላከል፣ ኢስላምን ለማስፋፋት፣ ከወገኖችህ ጎን ለመቆም ምን ድርሻ አለህ? ነፍሲያህንስ ለመታገል ቁርጠኛ ነህ ወይ? ለደካማ ወገኖችህስ ከልብህ አምርረህ ዱዓእ አድርገሃል ወይ? የምትችለውን ሳታደርግ ስለማትችለው ብትጮህ ጩኸትህ የቁራ ጩኸት ይሆናል። የምትችለውን ስትወጣ፣ ከዚያም በነፍስህ ጭምር ለመፋለም ቁርጠኛ ኒያ ቢኖርህ ጥረትህ ፅድቅ ነው። ምኞትህም ድንቅ ነው። አላህም የምኞትህን ይሰጥሃል።

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group