Translation is not possible.

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ትናንት ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ል ለ7 የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።ሰባቱ ምሁራን መካከል ስለ ፕሮፌሰር አሕመድ ሙስጠፋ ጥቅት ነገር...!

...

(ሀሩን ሚዲያ ጥቅምት 13/ 2016)

...

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትላንትናው እለት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸው ብቁ ምሁራን መካከል ፕ/ር አሕመድ ሙስጠፋ ይገኙበታል። ፕ/ር አሕመድ በሙያ ዘርፋቸው አንቱታን ያተረፉ ሊቅ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በትጋታቸው፣ ለሀገርና ለማህበረሰባቸው ባላቸው የላቀ አበርክቶ፣ በማህበራዊ ኃላፊነትና ለወጣቶች አርዐያ በመሆኑ ምስጉን ስብዕና የተላበሱ ናቸው። ከምሁራዊና ማህበራዊ አበርክቶዋቸው በጥቂቱ:

• በቲዮሬቲካል ኬሚስትሪ Ph.D ከኮንስቡሩክ፣ ኦስቲሪያ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል

• ከ27 በላይ የጥናትና ምርምር ጽሁፎችን በታወቁ ጆርናሎች አሳትመዋል

• በአርባምንጭ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ25 ዓመት በላይ አስተምረዋል

• አአዩ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆነው ለ8 ዓመታት አገልግለዋል፣ አሁንም የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ናቸው፡፡

• በአአዩ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ረዳትና ተጠባባቂ ኃላፊ ሆነው በተለያዩ ጊዜዎች አገልግለዋል

• የአፍሪካ የውሃ ማኔጅመንት ልህቀት ማዕከል ተጠባባቂ ኃላፊ ሆነው በተለያዩ ጊዜ አገልግለዋል

• የአፍሪካ የኬሚስትሪ ባለሙያዎች ማኅበር እንዲቋቋም አድርገው የማህበሩ የቦርድ አባል በመኾን አገልግለዋል፡፡

• የኦሬንጅ ኬሚካል ማስወገጃ እና የአፍሪካ አደገኛ ኬሚካል ማስወገጃ ማህበሮች የቦርድ አባል ናቸው

• በተለያዩ የግል ት/ቤቶች የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል

• መጂሊስ ጠንካራ ተቋም እንዲኾን እና ሙስሊሙ ማህበረሰብን ለማገዝ በግልና በጀመዓ ከፍተኛ የምክርና የሽምግልና ድጋፍ በተለያዩ ጊዜ አድርገዋል

• የተለያዩ ጀመዓዎች፣ ማህበሮችና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲቋቋሙና እንዲያድጉ ድጋፍ እያደረጉ ነው

• በቢላሉል ሐበሺይ የቦርድ አባል ኾነው ከ10 ዓመታት በላይ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ፕ/ር አህመድ ሙስጠፋ ለዚህ ስኬት በመብቃጣቸው እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።

...

¤መረጃው የሆራይዝን ሚዲያ ነው!

...

©ሀሩን ሚዲያ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group