Translation is not possible.

ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች ዘንድ የተሰራጨው ኒካህ ላሰረላት ሴት ቀለበት ማድረግ የሚባለው ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ይተገበር ያልነበረ ከክርስቲያኖች የተወሰደ ተግባር ነው።

የዘመናችን ሙሀዲስ የሆኑት ሸይክ ናሲረዲነል አልባኒ እንዲህ ይላሉ

"ይህ ተግባር ወደ ቀደመ (የክርስቲያኖች) ተለምዶ ይመለሳል። ሙሽራው በሙሽሪት የግራ እጅ አውራ ጣቷ ጫፍ ላይ ቀለበቱን ያደርግና በስመ አብ ይላል ከዛም አመልካች ጣቷ ጫፍ ላይ ያደርግና በወልድ ይላል ከዛም የመሀከለኛ ጣቷ ላይ ያደርግና በመንፈስ ቅዱስ ይላል በመጨረሻም አሚን በሚል ግዜ ከትንሿ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣቷ ላይ ያደርገውና በዛው ይቀራል።

ለንደን የሚታተም women የሚል ጋዜጣ (ቁ 19 1960 ገፅ 8) ላይ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ

Why is the wedding ring placed on the third finger of the left hand?

ለምንድነው የሰርግ ቀለበት በግራ እጅ ሶስተኛ ጣት ላይሚቀመተው?

በርእሱ ላይ መልስ የሚሰጠው Angela Talbot እንዲህ ብሎ

“it is said there is a vein runs directly from the the finger to the heart. Also,there is the ancient origin whereby the bridegroom placed the ring on the tip of bride’s left thumb,saying ; “in the name of the father” on the first finger, saying “in the name of the son “ on the second finger, saying ; “And of the holy ghost”,on the word “Amen” , the ring was finally placed on the third finger where it remained”

"ከዚህ ጣት ቀጥታ ከቀልብ የሚያገናኝ ደም ስር አለ ይባላል። ከዛም በተጨማሪ የቀደመ መሰረት አለው ካለ በሗላ ከላይ የጠቀስነውን በስምአብ...የሚለውን እስከመጨረሻው ጠቀሰ"¹⁶⁸

በዚህ ንግግር እንደምንረዳው ይህ ተግባር የመጣው ከክርስቲያኖች እንደሆነና ጥንታዊ የሆነ እምነታዊ መሰረትም እንዳለው ነው። ይህንን የሚጠቅሱም ብዙ ኡለሞች አሉ።

በመሆኑም

▪️ይህ ተግባር የክርስቲያኖች እምነታዊ መገለጫ ነው። ከነሱ መመሳሰል ደግሞ ከከባባድ ወንጀሎች ነው።

▪️ ይህን ቀለበት ግራ እጅ ከትንሿ ጣት ጎን ሚያደርጉበት ምክንያት ይህ ጣት ከልብ ጋር ግንኙነት አለው የሚል ከንቱ እምነት ይዘው ነው ይህ ደግሞ በእስልምና ቦታ የለውም

▪️ ብዙ ሰዎች ዘንድ ቀለበት ማሰሩ በመሀከላቸው ውዴታን ያመጣል የሚል እምነት አለ ይህም ከእስልምና አቂዳ ጋር ቀጥታ የሚጣረስ የሽርክ አይነት ነው።

▪️ አንዳንዶች ደግሞ ቀለበት ካለበሰ ወይም ካለበሰች ኒካው ትክክል አይመስላቸውም ይህም መሰረት የሌለው አጉል እምነት ነው።

▪️ ይህ ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ያልተለመደ ከክርስቲያኖች የተወረሰ ነው

▪️ አንዳንዶች ገና ሲተጫጩ ኒካም ሳያስሩ ወስዶ ቀለበት ያደርግላታል ይህ ደግሞ የተከለከለችን አጅነብይ ሴት እጅ መንካት ነው ያም ከባድ ወንጀል ነው።

እንዳጠቃላይ ለኒካህ ወይም ሰርግ ብሎ ቀለበትን መልበስ የሙስሊሞች ሳይሆን የክርስቲያኖች ሱና ነው።

ኢብን ኡሰይሚን ስለዚህ ሲናገሩ

"እኔ ማየው አነሰ ቢባል ይህ ተግባር የተጠላ ነው ይላሉ።”

ኢብን ባዝም ለሰርግ ብሎ ቀለበት ማሰር የሙስሊሞች ሱና እንዳልሆነ ይገልፃሉ። ሸይኽ አልባኒም እንደማይቻል ይገልፃሉ።

ከዛ ውጪ ባለ ሁኔታ ግን ለኒካህ አስበህ ሳይሆን እንዲሁ ቀለበትን በኖርማል ግዜ ብትለብስ ችግር የለውም። ለወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለበት አይፈቀድም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group