Translation is not possible.

በሆሳዕና ከተማ አንዳንድ የፕሮቴስታንት እምነት የመንገድ ላይ ሰባኪዎች ሙስሊሞች በሰላም እንደይንቀሰቀሱ እያወኩ መሆናቸው ታወቀ !

...

(ሀሩን ሚዲያ፦ጥቅምት 11/2016)

...

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ መንገዶች ላይ የሚሰብኩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አንድ ሙስሊምን አባት መንገዱን ዘግተው በማስገዳድ ጥቃት እንዳደረሱባቸው ተገልጿል።

...

በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከዚህ ቀደም በሙስሊሞች ላይ አዛን መከልከልን ጨምሮ የተለያዩ ጥቃቶች ሲፈጸም የቆዩ ሲሆን ሙስሊሞች በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ በግዳጅ እየያዙ ጫና እያደረጉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

...

መንግስት የዜጎችን የሃይማኖት መብት እና በሰላም የመንቀሳቀስ መብት ማስከበር ይጠበቅበታልም ተብሏል ።ይህ ድርጊት ከእለት ወደ እለት እየሰፋ የመጣ ድርጊት መሆኑንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group