7 month Translate
Translation is not possible.

#እህቴ ኑሮሽን ከሰው ኑሮ ጋር አታወዳድሪ!!መረጋጋትን ታጫለሽና..

አታይኝም እኔን እህትሽን ኢሰላሚክ ወይን ብለው 30ሺ አውጥተው ሲገዙ አየሁ ለፕሮግራማቸው እኔም ለምን ይቅርብኝ ብዬ 30ብሬን አውጥቼ የራት ፕሮግራሜን በወይኑ ፈታ በኮካ አስውቤዋለሁ!! ኸላስ

ምን ልልሽ ነው እህቴ የጓደኛዬ ባል ለሚስቱ ይሄን አደረገ ጎረቤት ቤታቼው ከኔ እጥፍ ያማረ ነው,, እያልሽ ኑሮሽን ከሰው ጋር እያወዳደርሽ ሰላምሸን አትጪ.. በአለሽ ነገር ተብቃቅተሽ ኑሪ ለቤቱ ለልጆቹ ደፋ ቀና የሚለውን ባልሽን ድካም ተረጂ ..ሁሌ ስታማሪ መስማቱ ለሱም ሰላም አይሰጠውም ትዳርሽም እድሜው ሊያጥር ይችላል .... እናም ብልህ ነው መሆን ያለብን

በመጅሊሳቼው ቤታቸውን ፏ አድርገው አየተን ከሆነ

እኛ በፍራሻችን ቤታችን ፏ አድርገን ማሰዋብ

45ሺ ብር የተገዛ ምጣፋቸውን አይተን ከሆነ ...የላስቲኩም ምጣፍ ይሁን ውልውል አድርገን አፅድተን ፍርሸርሸ ማድረግ ....እኛም ሌሎቹ የሚያገኙትን ደስታ እናገኛለን ብቻ ባለን ነገር በተሰጠን ስጦታ እንብቃቃ ብቻ!!

አላህዬ በሰው ሀያት ቀንተው የሞቀ ቤታቸውን ከሚያፈርሱት አያድርገን !!

Send as a message
Share on my page
Share in the group