Наган дахаан йохтахам.

#update

ኮልፌ ሎሚ ሜዳ አካባቢ በሚገኝ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት የሚያስተምሩ ሁለት ሴት  አስተማሪዎች ጅልባብ ለብሳቹ ማስተማር አትችሉም ብሎ የት/ቤቱ አስተዳደር አጸያፊ ቃላት በመናገር ጭምር  ክልከላ ለማድረግ ሞክሮ ነበር። ነገር ግን የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የወረዳው መጅሊስና የአዲስ አበባ መጅሊስ በመተባበር ጉዳዩ መስተካከሉን ዛሬ ገልፀዋል።

ሆኖም ግን ጉዳዩ ለጊዜው ቢፈታም ነገ ላይ በዚሁ ት/ቤት ወይም በሌላ ቦታ ላለመደገሙ ዋስትና የለም።

መፍትሄው ወጥ የሆነ ቋሚ ህግ ማስወጣት ነበር። ግና ኒቃብን እያቃለሉ ለጠላት በር ከፍተው በየቦታው ለሚጫር እሳት ሁሉ ውሃ ደፊ አደረጉን። አሁንም ከላይ ጀምሮ በቋሚነት ኒቃብና ጂልባብ የመልበስ ነፃነት በይፋ እንዲታወጅ መጅሊሱ የበኩሉን ድርሻ ቢወጣ እንዲህ በየ ት/ቤቱ እየዞሩ መቸገርም አይፈጠርም።

ያኔ ከልካይ ካለ በህግ ክፍሉ በኩል ቀጥታ ተጠያቂ የማድረግ ሥራ ተሠርቶ መቀጣጫ ማድረግ ይቻላል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group