Translation is not possible.

በወጣት ሺሀብ ሱሌይማን የተሰራ ኡርጂን የተሰኘ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ሞተር ሳይክል በኢትዮጵያ ተመርቶ ለገበያ ቀረበ።

...

(ሀሩን ሚዲያ፦ጥቅምት 13/2016)

...

የወጣቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሺሀብ ሱሌይማን የፈጠራ ውጤት የሆነው የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል አስፈላጊው የፍተሻ ስራ ተደርጎለት በኢትዮጵያ ውስጥ ተመርቶ ለገበያ ቀርቧል።

...

የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሉ በሰአት 60 ኪ.ሜ የመጓዝ አቅም ያለው ሲሆን አንድ ጊዜ ሙሉ ሀይል ቻርጅ ለማድረግ ስድስት ሰአት ይፈጅበታል ተብሏል።

...

የሞተር ጉልበቱ 1500 ዋት ሲሆን ያለ ቁልፍ መነሳት እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው።ሞተር ሳይክሉ ስርቆትን ለመከላከል የሚረዳ የማንቂያ ደውል(አላርም) የተገጠመለት ስለመሆኑ ተገልጿል።

...

የአንዱ ሞተር ሳይክል የመሸጫ ዋጋ 80 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ነው።ሞተር ሳይክሉን ወደ ስራ ለማስገባት ለአመታት ያክል የተለፋበት ስለመሆኑ የተነገረ ሲሆን ከካርበን ልቀት ነጻ የሆነና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ነው።

...

ከከባቢ ጋር ተስማሚ እና የኢትዮጵያን ስነ-ምህዳር ከግንዛቤ ባስገባ ዲዛይን የተመረተ ስለመሆኑም ተመላክቷል።

...

የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሉ በሀገር ውስጥ መመረቱ ኢትዮጵያውያን በአለም ላይ በቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው መውጣት እንደሚችሉ ምስክር ነው። የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ ውጤት ነውም ማለት ያስችላል።

...

ወጣት ሺሀብ ሱሌይማን የበርካታ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን ለቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ልዩ ፍቅር አለው።መሰል የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ይበራከቱ ዘንድ ለወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል።

...

©ሀሩን ሚዲያ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group