Translation is not possible.

✍️ሕይወት እንደ ሙስዐብ ከፈን ናት፡፡ እግር ቢሸፍኑ ጭንቅላት፤ ጭንቅላት ቢሸፈኑ እግር ይገለጣል፡፡ ፈተናዋ ያልቃል እንጂ አይጨረስም፡፡ ሜዳውን ብታልፍ ኮረብታዋ አለ፡፡ ‹ሀ› ስትል ‹ሁ› ይቀጥላል፡፡ ፊደሏን ብታጠናቅቅ ንባቧ ይከተላል፡፡ ድግሪዋን ጨረስኩ ስትል ማስተርሷ ይመጣል፡፡ የሰው ልጅ እስካለ ድረስ እንደተማረ ነው፡፡ ከዱንያ ምሉእነትን መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ በሷ ላይ ሞላለት የሚባለው ሰው ባለው ነገር ተብቃቅቶ ከልቡ ‹አልሐምዱ ሊላህ› ያለ ብቻ ነው፡፡ ዱኒያን “በቃህ” እንጂ “በቃኝ” ተብሎ የተሠናበተ የለም፡፡ ከዱኒያም ፍላጎቱን ሁሉ አሟልቶ የሄደ ፍጡር የለም፡፡

እድሜ ልክ ቢኖሩባት ዓለም ዘጠኝ ናት፡፡ የለፋላት አያገኛትም፣ ያገኛት አይዛትም፣ የያዛት አይጨብጣትም፣ የጨበጣት አይበላትም፣ የበላት አይጠግባትም፣ የጠገባት አይረካትም፣ የጀመራት አይጨርሳትም፡፡ ዱኒያ ጉዞ ስትሆን ሰዎች ሁሉ የቅርብ ወራጆች ናቸው፡፡🧡

Send as a message
Share on my page
Share in the group