Translation is not possible.

ኢየሱስ ሲመጣ "የእስራኤል/አይሁድ ንጉስ" ተብሎ ነው የሚመጣውና እስራኤላውያን ያሻውን ያክል ግፈኛ ቢሆኑም በግፋቸው ሳቢያ እንዲጠፉ አንመኝም፥ ምክንያቱም እነሱ ከጠፉ ኢየሱስ "ንጉስ" ተብሎ በትንቢቱ መሠረት የሚጠራበት ህዝብ አይኖርም ማለት ነው 🤦‍♂️ አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖቼ ሎጂክን አስገድዳችሁ የምትደፍሩበት መንገድ ያሳዝነኛል።

1/ ኢየሱስ እንደ እናንተ እሳቤ አምላክ እንደመሆኑ መጠን ንጉስነቱ ለአለም እንጅ ለእስራኤላውያን ብቻ አይደለም። ሲመጣ አሁንም እስራኤላውያን ጋ የሚነግሴ አህዛብ የማይመለከቱት ሰው ነው ብላችሁ ነው የምታምኑት?

2/ ይህ ማለትኮ የምበላበት ሳህን የፈለገ ቆሻሻ ቢያርፍበት በሱ ለመብላት ስለወሰንኩ ሳላጸዳው ከነቆሻሻው እበላበታለሁ እንደማለት ነው። ለኢየሱስ ያላችሁ አመለካከት በዚህ ግፍ የታጠረ ነው?

3/ ኢየሱስ ለንግስና ስያሜው ብቻ ተጨንቆ ያንን ሁሉ ግፍ የሚፈጽሙ ህዝቦችን /እሱን መስቀል ጨምሮ/ እንዲሁ በፍርደ ገምድልነት ችላ ይላቸዋል ብላችሁ ታምናላችሁ?

4/ ኢየሱስ እንደ እናንተ እሳቤ የዚህ ግፍና በደል አጽዳቂ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? ጽዮናውያን የሚሰሩትን ግፍ እናንተ ስትደግፉ አምላካችሁ ጋ ተመሳሳይ አፕሩቫል እንዳለ ታምናላችሁ ማለት ነው? ታዲያ እንዲያ ከሆነ ኢየሱስንም መግደላቸውም ልክ ነበር ማለት ነው?

Send as a message
Share on my page
Share in the group