Translation is not possible.

❤የነቢዩ (ﷺ) የኑሮ ሁኔታ እና ሥነ-ምግባር

°በላጭ_ሕዝቦች°

#ክፍል 2

በክፍል አንድ የተጠቀሱት ትእዛዞች በቁርኣን ውስጥ እጅግ ብዙ ናቸው። ትዕዛዛቱም የተላለፉት ሥርዓት ለማስያዝና ለመምራት ነው። መልካም ሥነምግባራቱን በመከተል ረገድም የመጀመሪያው እርሣቸው ናቸው። ከርሣቸውም ብርሃን ፈነጠቀ። በቁርኣን ተማሩና ሌሎችንም አስተማሩ።

...ለዚህም ነው ነብዩ ﷺ ሲናገሩ “እኔ የተላክሁት መልካም ሥነምግባራትን ላሟላ ነው።” ብለዋል። (አሕመድ፣ አል-ሓኪም እና በይሀቂ እንደዘገቡት) በዚህም የተነሳ ባህሪያቸው የተሟላና ሙሉ በሙሉ ያማረ ሆነ። አላህም ውዳሴ ቸራቸው

وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ

“አንተ በታላቅ ሥነምግባር ላይ ነህ።” (አል-ቀለም ፡ 4) በማለት።

ለአላህ ጥራት ይገባው። እጅግ ታላቅ የሆነ አምላክ። እጅግ የሚወደስ የሚቀደስ ጌታ!። እዝነቱ ሁሉን ያካበበ ነው። ችሮታው የገዘፈ ነው። ምርጥ ሥነምግባራት ራሱ ሠጣቸውና መልሶ ያወድሳቸዋል። በመልካም ሥነምግባር ያስዋባቸው እርሱ አላህ (ሱ.ወ.) ነው። መልሶ ሲያወድሳቸው በርግጥ የሚገርም ነው። “አንተ በታላቅ ሥነምግባር ላይ ነህ።” በማለት።

ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) አላህ (ሱ.ወ.) መልካምና ምርጥ ሥነምግባራትን እንደሚወድ መጥፎዎቹን እንደሚጠላ ተናግረዋል። ከመልካም ሥነምግባራት መካከል -ከሰዎች ጋር በመልካም ሁኔታ መኗኗር፣ አብሮ በመሥራት ሂደት ጥሩ ሰው መሆን፣ገርና ለስላሳ መሆን፣ ለፍጥረታት ሁሉ መልካም መሥራት፣ የተራበን ማብላት፣ ለሚያውቁትና ለማያውቁት ሁሉ ሠላምታ ማቅረብ፣ መጥፎም ይሆን ጥሩ የታመመን መጠየቅ፣ የሙስሊምን ጀናዛ ወደማረፊያ መቃብሩ መሸኘት፣ ሙስሊም ለሆነውም ላልሆነውም መልካም ጎረቤት መሆን፣ ትልቅ ሰውን ማክበር፣ የጠሪን ግብዣ መቀበልና ለሱም ዱዓ ማድረግ፣ ይቅር ማለት፣ ሰዎችን ማስታረቅ፣ ቸርነት፣ ልግስና፣ጥፋትን ማለፍ፣በሠላምታ መቅደም፣ ቁጣን መዋጥ፣ ሰዎችን ይቅር ማለት፣ እስልምና ከከለከለው ነገር ሁሉ መራቅ፣ ለምሳሌ ከውሸት፣ ከስስት፣ ከንፉግነት፣ ከጭካኔ፣ከተንኮል፣ከክህደት፣ ከሀሜት፣ ሰዎችን ከማጣላት፣ ዝምድናን ከመቁረጥ፣ ከመጥፎ ባህሪ፣ከኩራት፣ከጉራ፣ከማስመሰል፣ከመንጠባረር፣ ከመመፃደቅ፣ ከመጥፎ ነገር እና መጥፎ ከመሆን፣ከጥላቻ፣ከምቀኝነት፣በመጥፎ ገድ ከማመን፣ከግፍ፣ድንበር ከማለፍ፣ በመጥፎ ገድ ከማመን፣ ከግፍ፣ ድንበር ከማለፍ፣ድንበር ከማለፍ፣ ከበደል

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group