የወንጀል ጣጣ
==========================
ሁላችንም እንደምናውቀውየሰው ልጆች አባት የሆኑት አደም (ዐ•ሰ) ከውቢቱ ሀገር ጀነት ያስወጣቸው እና ወደ አድካሚዋ ምድር የመጡበት ምክኒያት ወንጀል ነው።
እንድሁም ኢብሊስ ከነበረው ደረጃ በመዋረድ ለዘለዓለም የተረገመ የሆነው በወንጀል ነበረ።
በተለያዩ የወንጀል አይነቶች #አሏህን በማስቆጣታቸው #አላህም በተለያየ መንገድ እንዳጠፋቸው እና መቀጣጫ እንዳደረጋቸው ቂሷቸውን በቁርአን የተረከልን ቀላል አደሉም።
=============================
#ዓድ እና የ#ሰሙድ ህዝቦች እንደት እንዳ ጠፋቸው ይነግረናል።
فأما ثمود فأهلكوا با الطاغية* وأما عاد فأهلكو بريح صرصر عاتية * سخرها عليهم سبع ليال وثمانية ايام حسوما فتر القوم فيها صرعي كأن هم اعجاز نخل خاوية *فهل تري لهم من باقية*
#ኑህ ህዝቦችም እንደት እንደተጠፉ ሰምተናል።አላህ እንዲህ ይላል
وقيل يا أرض إبلعي ماء كي ويا سماء اقلعي وغيض الماء وقضي الامر وستوت علي الجو وقيل بعدا لظالمين *
ስለ #ሹዐይብ ህዝብም የሚለው አለው
ولما جاء امرنا نحينا شعيبا والذين امنوا معه برحمة منا واخذت اللذين ظلموا الصحية فاصبحوا في ديارهم جاثمين *كأن لم يغنوا فيها الا بعدا للظالمين*
#ሷሊህ ህዝቦችም ከተጠፉት ነበሩ። አላህ እንዲህ ብሏል።
فلما جاء امرنا نجينا صالحا والذين امنوا معه برحمة منا ومن خزي يومءذ ان ربك هو القوي العزيز*
ፈርዑንም አጋሮቹም ፣ቃሩንም እስከ ንብረቱ በየ ክፍለ ዘመኑ ማን አለብኝ ?ሲሉ የነበሩት ሁሉ ግዚያቸው ሲደርስ #አላህ ተበቅሏቸዋል።
#እኛም ወንጀልን በተዳፈርን ቁጥር ያለፉት ህዝቦች እጣ ፈንታ እንደማይደርሶብን የተሰጠን ዋስትና የለም። አሰከመጨረሻው አላህ ባያጠፋን እኳ ወንጀላችን እራሱ ያጠቃናል።
#ወንጀል #የሚያስከትለው #አደገኛ #ተስዕኖ
1/ወንጀል ፀጋዎችን ያጠፋል ።
ዐሊይ አረንድህ ብለዋል።
ما نزل بلاء الا بذنب ولا رفع الا با التوبة
2/#አላህም እና ሰዎች ክብር ጋር የነበረው ክብር ይቀንሳል።
3/ዐቅል ያጎድላል።
4/በባሪያው እና በአላህ መካከል የነበረውን ቅርርብ ያቆራርጣል።
5/የእድሜን በረከት ያነሳል።
6/የሪዝቅን በረከት ያነሳል።
7/የእውቀትን፣ የስራን በረከት ያጠፋል።
8/ያከብሩት ይፈሩት የነበሩ ሰዎች እንዲነሳሱበት ያደርጋል።
9/ቀለብን ያደርቃል።
10/በመጨረሻም አላህ ጋር ያጣላል። ለጀለነምም ሊዳርገን ይችላል።
 
 
✍️mohammedmekin Hussein
Send as a message
Share on my page
Share in the group