Translation is not possible.

አላህ ሰዎችን በአንድ ጥፋት አያዋርድም። ለሰውም አያጋልጣቸውም። በዚያ ድርጊት ላይ የሚመላለስ ቢሆን እንጂ። ሁላችንም ወንጀል ሰርተናል። ብዙዎቻችን ወንጀላችን በእኛና በጌታችን አላህ(ሱወ) ዘንድ ነው። ሆኖም አላህ ይጠብቀንና ከመደጋገማችን ብዛት አላህን ረስተናል። የአላህ(ሱወ) ዝምታ አላህ የሌለ እስኪመስለን ድረስ ሆኗል። ቀልባችን ደርቋል። በወንጀል ላይ በየዕለቱ ስንዘወትር ብዙ የተውባ እድሎችን አበላሽተን በዱንያም በአኸራም ከመዋረድ አላህ ይጠብቀን! ወደርሱም ይመልሰን!

ድርጊቱ በኸሊፋው ዓሊ ኢብን አቢ ጣሊብ(ረዓ) ዘመን የተፈጸመ ነው። ሰውየው ሰርቆ ይያዝና እጁ እንዲቆረጥ ይፈረድበታል። እጁ ሊቆረጥ ሲል ያው የሌባ አይነደረቅ ነበርና "ያ አሚረል ሙዕሚኒን እኔኮ የመጀመሪያ ጊዜ መስረቄ ነው" ይላል። በዚህ ጊዜም አሊ ፈርጠም ብለው እንዲህ አሉት "አትዋሽ! የመጀመሪያ ስርቆትህ ቢሆን ኖሮ አላህ አያዋርድህም ነበር። ከዚህ በፊት የሰረቅከው ስርቆት ይኖራል" ሲሉት እጁ ሊቆረጥ የተዘጋጀው ሌባም ቀልቡ ደንገጥ ብሎ እንዲህ አለ፦ "ወላሂ እውነት ነው የተናገርከው! መቆረጤ ካልቀረማ እውነቱን ልናገር። አሁን የሰረቅኩት ለ21ኛ ጊዜ መስረቄ ነው" ብሎ አምኖ የሸሪዓው ህግ ሊፈጸምበት ችሏል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group