Translation is not possible.

ኑዕማን ብኑ ሙቀሪን ረዲየላሁ ዐንህ

~

ጀግና የጀግና ቤተሰብ ናቸው። እሳቸውን ጨምሮ ሰባት ወንድማማቾች ሁሉም የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሐቦች ሁሉም ሙሃጂሮች ናቸው። እንዲህ አይነት ሁኔታ ከነሱ ውጭ ላለ የለም። ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦

"ለኢማን ቤቶች አሉት። የሙቀሪን ቤት ከኢማን ቤቶች ውስጥ ነው።"

ኑዕማን ብኑ ሙቀሪን ዒራቅን ለመክፈት በተደረጉ ተከታታይ ዘመቻዎች ላይ ግንባር ቀደም ነበሩ። ዛሬ ኢራን ውስጥ የምትገኘዋን አስፈሃንን በድል የከፈቷትም እሳቸው ናቸው። በመጨረሻም በ21ኛው አመተ ሂጅራ በነሃወንድ ጦርነት ላይ ወድቀዋል። ረዲየላሁ ዐንሁ ወአርዷህ። ሞታቸው ለኸሊፋው ዑመር ሲደርስ ከባድ መርዶ ነበር። ዑመር ሚንበር ላይ ወጥተው ለህዝብ አረዱ። እራሳቸውን በእጃቸው ይዘው ተንሰቅስቀው አለቀሱ። ሁሉንም አላህ ይውደድላቸው።

[አልኢስቲዓብ፡ 10/319] [አልኢሷባህ፡ 10/170]

Ibnu Munewor

=

* የቴሌግራም ቻናል

https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦

https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo

* ፌስቡክ

https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW

Send as a message
Share on my page
Share in the group