Translation is not possible.

ሱመያ ...  ያሲር ... ሙስዐብ ... አነስ ኢብኑ ነድር...  ሐምዛ...  ሰዕድ ኢብኑ ረቢዕ...  ዐምር ኢብኑል ጀሙሕ  ሁላቸውም የኢስላምን የበላይነትና መደላደሉን ሳያዩ ነበር የተሰውት... 

የሀገራትን በዑመር መከፈትና የኻሊድን ድል አላዩም ነበር ....

ረቢዕ ኢብኑ ዓሚር የፋርሶች የጦር አዛዥ ሩስቱም ፊት በዲኑ ኩራት እየተሰማው ሲቆም አላዩም ነበር ...

ሀሩነ ረሺድ ደመናን እያናገረ «የትም ዝነቢ ምርትሽ ይደርሰኛል» ሲል አላዩም .....

እነርሱ ያደረጉት ነገር ቢኖር መንገዱን መጀመር ብቻ ነበር ..

መንገዱን ጀመሩት...  በመጀመሪያው ጅማሮ ሞቱ። መጨረሻውን አልደረሱትም ነበር።የጀመሩትን መንገድ ፍሬ አላዩትም ነበር። ረዲየላሁ ዐንሁም! 

ደከሙ፣ ታገሉ፣ ተሰቃዩ፣ በፈተናውና በደካማነቱ ጊዜ ታገሱ ...

ስለዚህ ስለ መንገዱ  መጨረሻ አትጠይቅ ! ...

ትልቁ ነገር አንተ በመንገዱ ላይ መሆንህ ነው ፣ አሳሳቢው ነገር አንተ በመንገዱ ላይ ፀንተህ እስልምናህን አጥብቀህ መያዝህ ነው።

በመንገዱ ላይ እስካለህ ድረስ መጀመሪያው ላይ መካከሉ ላይ ወይም መጨረሻው ላይ መሞትህ አይጎዳህም! 

ትልቁ ጉዳይ አላህ እንዲህ ካላቸው ሰዎች መሆንህ ነው፦  

«ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ፡፡ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አልለ፤ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አልለ፡፡ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም፡፡» (አል አሕዛብ 23)  

እኛ በመንገዱ ላይ እንጓዛለን፣ አላህም እንዲቀበለን ተስፋ እናደርግበታለን፤ አላማችን የመንገዱ ጫፍ መድረስ አይደለም።አላማችን በመንገዱ ላይ መሞት ብቻ ነው። ዲኑን ጠባቂው አላህ ነው።

በሁሉም ጉዳይ ላይ በሁሉም ጊዜና ሰአት ውስጥ  ኒያችንን እናድስ!  መጓዥያችን መች እንደሆነ አናውቅም! 

አላህ እንዲጠቀመን እንጅ እንዳይቀይረን እንለምነዋለን! ኢስላም የበላይ ሆኖ አይናችንን እንዲያረካም እንማፀነዋለን!

አላህ ሆይ! ምራን፣ በኛም ሌሎችን ምራ ! ለፍጡራኖችህም መመራት ሰበብ አድርገን! 

(ከፌስቡክ የዐረብኛ ፖስት በድሮን በረር የተተረጎመ)

ቴሌግራም ፦ t.me/ismaiilnuru

Send as a message
Share on my page
Share in the group