لا يمكن الترجمة

#የዚች_ዓለም_የሰው_ሁለት_ገፅታዎች

▬▬▬▬▬▬☝️▬▬▬▬▬▬

#ጅብ ምግብ በማይኖርበት ሰዓት ጓደኛ የለውም፤ ብቻውን ይንቀሳቀሳል ። ምግብ ሲያገኝ ግን ጓደኛውን ሁሉ ጠራርቶ

አብሮ ይበላል። ፈረንጆች ኑሯቸው ግላዊ ነው። ጀሌና ጓደኛ አያበዙም። የተሻለ ደረጃ ሲደርሱ ሕዝባቸውን የሚጠቅም

ታሪክ ጥለው ያልፋሉ። አሁን የምንጠቀምበት ከልብስ ስፌት

ማሽን እስከ አውሮፕላን ድረስ ምንም እንኳን የፈጠሩት ሌሎች ቢሆኑም ያበለፀጉት ግን ፈረንጆች ናቸው። በዚህም ምንም እንኳን በመንፈስ የዘቀጡ ቢሆኑም በቁሳቁስ ግን እጅጉን ከፍ በለዋል።

➾➾➾➾🤫

#ውሻ ምግብ በማይኖርበት ሰዓት ጓደኛው ጋር በፍቅር

ይጫወታል። ምግብ ሲያገኝ ጓደኛውን ነክሶ ያባራል።

ሲጠግብ ለጓደኛው አይሰጥም፤ ቆፍሮም ይቀብረዋል።

አብዛኛው የሀበሻ ጓደኝነት ሲቸግር ብሶት ለማውራትና ለማማት ፍቅር ተላብሶ ጓደኝነት ይመሠርታል። ሲያልፍለት ግን የችግር ቀን ጓደኛውን ይረሳዋል፤ መቅረብም አይፈልግም ። አይረዳዳም። ሌላውን እየጠላ እራስ ወዳድነትን ያፀባርቃል። ራሱን ብቻ ማደለብ። በወንድሙ ጫንቃ ላይም መቆምን ይሻል።

ስለዚህ ወገኔ ለጥፋት በመንጋ ሳይነዱ ለብቻቸው የተመስጦ ጊዜ ወስደው ለዚህ ሚስኪን ሕዝብ የሚጠቅም ስራ እንስራ።

➾➾➾➾🤫

ወገን እመነኝ ጊዜው ሲፈጥን፣ ቀኑም ሲመሽ፣ ንጹሁም ሲበላሽ፣ የተበላሸው ሲበዛ ፣ እውነት በውሸት ስትሽፈን... ተስፋ አትቁረጥ ቋሚ የለም ሁሉም ያልፋል።

#ኃለኞች #ከፊት #ፊተኞች #ኃላ #መሆኑ #አይቀሬ...

image
أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة