Translation is not possible.

#የመጀመሪያው_ሶፍ (#ረድፍ) #ትሩፋትና_ሶፎችን #መሙላትና_መጠጋጋት_ስለመታዘዙ

#ክፍል_13

#ሐዲሥ 194 / 1094

ዓኢሻ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ “አላህና መላእክት (ከኢማሙ) በስተቀኝ በኩል ላለው የሶፍፎች ክፍል ሶለዋት ያወርዳሉ።” (አቡ ዳውድ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ከኢማሙ በስተቀኝ በኩል መሆን ሱንና ነው።

2/ መስጊድ ስንደርስ በስተቀኝም በስተግራም በኩል ክፍተት ካየን በስተቀኝ በኩል ያለውን መሙላት ይበልጣል።

3/ ስለዚህም በደረጃ ከኢማሙ አቅጣጫ መሆን ከሁሉም ይበልጣል። በሌላ ሐዲሥ እንደተገለጸው። ከዚያም በስተቀኝ በኩል ያለው ይቀጥላል። በስተግራ በኩል ያለው የሦስተኝነትን ደረጃ ይይዛል።

4/ ከአሁን በፊት እንደተገለጸው የአላህ ሶለዋት ማውረድ እዝነቱንና ረድኤቱን ማስፈኑ ሲሆን የመላእክት ሶለዋት ደግሞ ዱዓ ማድረጋቸውና ምሕረት መለመናቸው ነው።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

Muslim ሙስሊም | UmmaLife
ummalife.com

Muslim ሙስሊም | UmmaLife

Send as a message
Share on my page
Share in the group