Translation is not possible.

ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐቢይ!

~

ሶሐቢዩ ሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፡-

በአንድ ወቅት ዑመር ብኑል ኸጧብ ከነቢዩ (ﷺ) ቤት ሊገቡ ፍቃድ ጠየቁ፡፡ ከነቢዩ (ﷺ) ዘንድ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያወሩ ሴቶች ነበሩ፡፡ የዑመርን ድምፅ ሲሰሙ ሒጃባቸውን አስተካክለው ሊለብሱ ተሯሯጡ፡፡ ረሱል (ﷺ) እየሳቁ ለዑመር እንዲገቡ ፈቀዱላቸው፡፡

ዑመር፡ “አላህ ጥርስህን ያስቀው የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሏቸው፡፡

ነብዩ (ﷺ)፡ “እነዚህ እኔ ጋር የነበሩ ሴቶች ገረሙኝ፡፡ ድምፅህን ሲሰሙ ወደ ሒጃባቸው ተሯሯጡኮ” አሉ፡፡

ዑመር፡ “አንተ ነህ ልትከበርና ልትፈራ የሚገባህ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!!” ካሉ በኋላ “እናንተ የነፍሶቻችሁ ጠላቶች! እኔን ትፈራላችሁ የአላህ መልእክተኛን አትፈሩምና?!” አሉ ለሴቶቹ።

ሴቶቹ፡ “አዎ ከረሱል (ﷺ) ይልቅ አንተ ደረቅና ሃይለኛ ነህ” አሉ፡፡

ከዚያም ረሱል (ﷺ) ለዑመር እንዲህ አሏቸው:– “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ! ሸይጧን በአንድ መንገድ ላይ በጭራሽ አያገኝህም፣ መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ ቢሄድ እንጂ!” [ቡኻሪ፡ 3294] [ሙስሊም፡ 2396]

ይሄ ሐዲሥ ለዑመር ጠላቶች ምቾት የሚነሳ ነው፡፡ ሺዐዎች የዑመር ስም ሲነሳ በጥላቻ እብደታቸው እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ድረስ ይሄ ነገር በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እ.ኢ.አ በ2005 ኢራቅ ውስጥ 15 ሰዎች ስማቸው ዑመር ስለሆነ ብቻ በሺዐዎች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ በርካታ ዑመሮች በሌላ ሳይሆን በስማቸው ብቻ ከስራ እንደተባረሩ ተነግሯል፡፡ ይሄ ለዑመር ያላቸው ጥላቻ እጅግ የመረረ እንደሆነ የሚያመላክት ነው።

ሌላ ነገር፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ﷺ) መስጂድ ካሉት በርካታ በሮች ውስጥ አንዱ “ባቡ ዑመር" ነው፣ "የዑመር በር”፡፡ ታዲያ ሺዐዎች ምን አሉ? “ለዑመር ካለን ጥላቻ የተነሳ ወደ መስጂዱ ስንገባ በዑመር በር በኩል አንገባም” አሉ። ይህንን የሰማ አንድ ሸይኽ ምን አለ ታዲያ? “ረዲየላሁ ዐንከ ያ ዑመር! ሸይጧን በህይወትህ ሳለህ ብቻ አይለም ሞተህም ይሸሽሃል!”

አላሁ አክበር!!!

(ኢብኑ ሙነወር፣ 03/02/2005)

#islam #gaza #ислам #хадисы #Коран #quran #islamedia #Палестина #إسلاميواليت #коран #إسلاميديا #Ислам #إسلاميكوين #сунна #дуа #акыда #хадис #рамадан #Рамадан #намаз

Send as a message
Share on my page
Share in the group