بسم الله الرحمن الرحيم
المَوتُ بابٌ وَكُلُّ الناسِ داخِلُهُ
فَلَيتَ شِعرِيَ بَعدَ البابِ ما الدارُ
الدارُ جَنَّةُ خُلدٍ إِن عَمِلتَ بِما
يُرضي الإِلَهَ وَإِن قَصَّرتَ فَالنارُ
هُما مَحلاَّن ماللناس غيرهما
فانظُر لِنفسِك ماذا أنت تَخْتَار
ሞት በር ሲሆን ሁሉም ሰው ገቢው ነው
አይ ዋ ፀፀቴ ከሞትስ በኋላ ሀገሩ ምንድን ነው?
ስራችን ከሆነ አላህ የሚወደው
ሀገሩ ጀነት ነው አትክልት የሞላው
አላህን በማመፅ ከሆነ የኖርነው
ከሞትን በኋላ ሀገሩ እሳት ነው
ከሞት ኋላ ያሉት ሁለት ቦታ ናቸው
ጀነት ወይ ጀሐነም ሶስተኛ የልላቸው
ሌላ ቦታ ምርጫ ለሰወች የልላቸው
ለራስህ አስተውል የቱን ነው የመረጥከው?
ይሄ ሞት የሚሉት የማይዝዘጋ በር
ስንቱን ሰው ወሰደው እዚሁ እኛ ሰፈር
ስንቱን ወዳጅ ዘመድ አስገባ ከ-አፈር!!
ማምለጫ የሌለው የእኩልነት አድማስ
ሀብታም ድሀ ሳይል ሁሉን የሚያድዳርስ!!
ስንቱን ባለ-ጉልበት በቅፅበት የሚጥል
ደካማ ነው ብሎ ልለፈው የማይል
ሀብታም በገንዘቡ ሊያመልጠው የማይችል
ሞት አንገት ይደፋል ሁሉንም በእኩል!!
እድሜ ገደብ የለው መምጫው አይታወቅ
ድንገት ከተፍ-ብሎ አላማን የሚሰርቅ!!
አይ ሞት !!...
አይ ሞት... የሁሉ አባት፣የሁሉ ሰው ድርሻ
ኧረ ገና ልጅ ነኝ...ተብሎ የሌለው መሸሻ!!
ዛሬ... እኔን አልፎ ሰንቱን ሰው ጠለፈው
አልሃምዱሊላህ...አልኩ የዛሬን ቀን ሳልፈው
ግን ለካስ...ነገ ተራው የራሴ ነው!!
ሌላውን ሲወስድ ዛሬ እኔን ያለፈኝ
ነገ ሌላን አልፎ ራሴን ሊወስደኝ!!
የማይቀረው ቀኔ፣ ሞቴ የኔ ድርሻ
ጥም ቆራጩ ቀኔ የኔ መጨረሻ!!
ምን ማምለጫ አለኝ ኪታቡ ተፅፎ
ሞቴ ተወስኖ ሁሉ ነገር አልፎ!!
ብቻ ኢላሂ....
እኔ ከንቱ ሰው ነኝ እዝነትክን የምሻ
ከአንተ ራህመት ውጭ የሌለኝ መሸሻ!!
በዱኒያ ብልጭልጭ አይኔን የተነካሁ
በወንጀል ሰምጨ አኼራን የረሳሁ!!
ልበ-ደረቅ ሆኘ ምክር የማይገባኝ
ከአንተ አምልኮ ይልቅ ስሜት የማረከኝ
በወንጀል ሰምጨ ዱኒያ ያደከመኝ
ምህረትን ፈላጊ ደካማ ባሪያህ ነኝ
አወ ያ ኢላሂ.... ምህረት ፈላጊ ነኝ!!
ወንጀሌ ቢበዛም ከባህር አረፋ
ከጌታየ እዝነት እኔ አልቆርጥም ተስፋ!!
ምህረትህን ከጃይ ነኝ ሰነፉ ባሪያህ
ጌታየ ሸፍነኝ በሰፊው እዝነትህ!!
ከሞቱ አሟሟቱ እንደሚሉት አበው
ያአላህ፣ ያረቢ ሞቴን አሳምረው!!
መንገዲህን ምራኝ ሰጥተህ እስቲቃማ
ያረቢ ወፍቀኝ መልካሙን ኻቲማ!!
✍Ibnu Ahmed(አቡል_ፋሩቅ)