Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

የነፃነት ቀንዲል  የመስዋዕት ፍሬ

  የልቅና ሚስጥር  የደግነት ኩሬ

  የስልጣኔ ምንጭ  የጥበብ ከፍታ

ቀዳሚዋ ቂብላ     የጀሊል ስጦታ፡፡

ኡመር ያስከበሩሽ   የኸጣቡ ጀግና

ያላቁሽ በጥበብ   በክብር በዝና

ልዑል ሠላሀዲን  የአዩቦች ወራሽ

በታሪክማህደር ላይ  በክብር ያስጠራሽ

የአይናችን ብሌን    የልብም ትርታ

አሏህ ይመልስሽ  ከሚገባሽ ቦታ፡፡

አለም ጆሮ ዳባ ቢልሽ  ብታጪ ነፃነት

ከላይሽ ቢያንዣብብ  የመደፈር ሀፍረት

በገዛ ርስታቸው   ልጆችሽ ቢናቁ

ጊዜ በሾመው ባለሟል  በጨካኝ ቢጠቁ

የትንሳዔሽ ችቦ   አንድ ቀን ይበራል

የነገሠው ዙልምም  ቀስ በቀስ ይጠራል

ፊዳ መሆን ባልችል  መጥቼ ከደጅሽ

ልቤ ካንቺ ጋር ነው  የሀበሻው ወዳጅሽ፡፡

🇯🇴🇪🇹🇯🇴🇯🇴🇪🇹🇪🇹🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас