Qumuqta qilghuchi yo'q.

ለስላስያዊያን ...

በአላህ ስም እጅግ በጣኝ ሩኋሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው ።

አንቢያዕ 21:22

لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡

ደግሞም፥ “ነፍሴ እስከ "ሞት" ድረስ እጅግ አዘነች፤ እዚሁ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው። ጥቂት ዕልፍ ብሎም በምድር ላይ በመውደቅ፥ ቢቻል ሰዓቱ ከእርሱ እንዲያልፍ "ጸለየና"፥ “አባ፤ አባት ሆይ፤ ሁሉ ነገር ይቻልሃልና ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን "የእኔ ፈቃድ" ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ።

የማርቆስ ወንጌል 14:34-36

በዚህ ክፍል በፈቃድ መለያየታቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል እንግዲህ ወልድ የራሱ ፈቃድ እንዳለው ያሳያል "የእኔ ፈቃድ" እንደናንተ እሳቤ ፈጣሪ ያላችሁት አብ ፈቃድ "የልጁን እየሱስን ሞት ይፈልጋል" ወልድ ግን "ሁሉ ነገር ይቻልሀልና ጽዋውን ከእኔ አርቅ" ብሎ ይለምነዋል ሁሉን ቻይ አምላክ ግን ሊያድነው አልቻለም ነው ?! ....

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የየራሳቸው እውቀት ፈቃድ ስሜት ካላቸው ! በእውቀት በስሜት በፈቃድ ከተለያዩ ? ለምሳሌ:- አብ ዛፍ አረንጎዴ እንዲሆን ቢሻ ወልድ ሰማያዊ እንዲሆን ሽቶ በሚፈጥሩት ነገር ሊቃረኑ ይችላሉ ወይስ አይችሉም ?!....

ሙዕሚኑን 23:91

مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group