Translation is not possible.

❤የነቢዩ (ﷺ) የኑሮ ሁኔታ እና ሥነ-ምግባር

°በላጭ_ሕዝቦች°

#ክፍል 1

አላህ (ሱወ) በቁርኣኑ ነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ሥርዓት ሲያስተምራቸው፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ አላህ (ሱ.ወ.) በብዛት በመዋደቅና በመተናነሳቸው ይታወቃሉ። በመልካም ሥርዓትና ምርጥ ሥነምግባር ያስውባቸው ዘንድ ዘወትር አላህን ይለምናሉ። ዱዓእ ሲያደርጉም እንዲህ ይሉ ነበር “አልላሁምመ ሐስሲን ኸልቂ ወኹሉቂ .../ አላህ ሆይ አፈጣጠሬንም ባህሪዬንም አሳርምርልኝ።” (አሕመድ ዘግበውታል) እንዲህም ይሉ ነበር “አልላሁምመ ጀንኒብኒ ሙንከራት አል-አኽላቅ አላህ ሆይ መጥፎ ባህሪዎችን አርቅልኝ፡፡” (ቲርሚዚ እና አልሓኪም እንደዘገቡት) አላህም ዱዓቸውን ተቀበላቸው። እሱ /እድዑኒ አስተጂብ ለኩም/ “ጥሩኝ ምላሽ እሠጣችኋስሁ” (ጋፊር ፡ 60) ብሏልና። ቁርኣን አወረደባቸውና ሥነ-ምግባራትን አስተማራቸው። በዚህም ምክንያት “ባህሪያቸው ቁርኣን ነበር። ቁርኣን ያዘዘውን ይታዘዛሉ፤ ከከለከለው ይከለከላሉ።” ለምሳሌ፦

”خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ“

“ገርን ጠባይ ያዝ፡፡ በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው፡፡” (አል-አዕራፍ፡ 199)

” ۞ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ“

“አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡” (አን-ነኽል:90)

”...وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

“...በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ፡፡ ይህ በምር ከሚያዙ ነገሮች ነው፡፡”(ሉቀማን:17)

”... فَاعْفُ عَنْهُمْ وَاصْفَحْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ“

“....ከእነርሱም ይቅርታ አድርግ እለፋቸውም፡፡ አላህ መልካም ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡” (አል ማዒዳህ ፥13)

”...ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ“

“ ...በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ጸባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር፡፡ ያን ጊዜ ያ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይኾናል፡፡ (ፉሲለት ፡ 34)”

”.... وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ“

“....ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡” (አሊ ዒምራን ፡134)

”...اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِّنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ ۖ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ ...“

“...ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡...” (አል-ሑጁራት ፡ 12)

የዚህ ዓይነቶቹ ትእዛዞች በቁርኣን ውስጥ እጅግ ብዙ ናቸው። ትዕዛዛቱም የተላለፉት ሥርዓት ለማስያዝና ለመምራት ነው። መልካም ሥነምግባራቱን በመከተል ረገድም የመጀመሪያው እርሣቸው ናቸው። ከርሣቸውም ብርሃን ፈነጠቀ። በቁርኣን ተማሩና ሌሎችንም አስተማሩ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group