بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله وحده عالم الغيب والشهادة والصلاة والسلام علي من لانبي بعده
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ አልሀምዱ ሊላሂ እስልምናን ከሌሎች ሀይማኖት አስበልጦ ለሰጠን ከዚያም በተውሂድ ላዘዘን እንዲሁም ከሽርክ ላስጠነቀُ۟ቀን። አላህ እንዲህ ይላል" ِ ۗ ٱلْيَوْمَ يَئِسَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن دِينِكُمْ فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَٱخْشَوْنِ ۚ ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًۭاۚ ِمٌ ዛሬ እነዚያ የካዱት ከሃይማኖታችሁ ተስፋ ቆረጡ፡፡ ስለዚህ አትፍሩዋቸው፡፡ ፍሩኝም፡፡ ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ። (ማኢዳ) وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ( አል ኢምራን) أَفَغَيْرَ دِينِ ٱللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُۥٓ أَسْلَمَ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ طَوْعًۭا وَكَرْهًۭا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ
በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ፤ በውድም በግድም ለርሱ የታዘዙ ወደርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ (ከሓዲዎች) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን አላህ የመረጠልን ሀይማኖት ኢስላም ተውሂድ ሆኖ ሳለ እኛ ግን "በተቃራኒው ኩፍር ወይም ሽርክ ላይ ተዘፍቀናል። ይህም ከዱንያ ሽንጋይ ነገሮች በአንዱ ተለክፈን ነው ከነዚህም መካከል የጠንቋይ ሽንገላ ይገኝበታል። ቀድሞውኑ ጠንቋይ ጋር መሄድ ሀራም ነው ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ"من أتي كاهنا فصدقه بما يقلو فقد كفر بما أنزل علي محمد صلي الله عليه وسلم"
"ጠንቋይን(የሩቅ ሚስጥር(ገይብ) አውቃለሁ የሚልን) የመጣ እንዲሁም ጠንቋዮ የነገረውን እውነት ብሎ የተቀበለ በርግጥ በሙሀመድ ላይ በተወረደው ክዷል"
በሌላሀዲሳቸው ደግሞ እንዲህ ይሉናል" من أتي عرافا فسأله عن شيء لم تقبل له صلاة أربعين يوما "አዋቂ ነኝ ብሎ የሚሞግትን(ሚስጥር ፣የጠፋነገር፣እንዲሁም ወደበፊት የሚከሰቱ ነገሮችን አውቃለሁ የሚል)ን የመጣ እንዲሁም ስላንዳች ነገር የጠየቀው(እውነት ብሎ ባይቀበልም) የአርባ ቀን ሰላቱ ተቀባይነት አይኖረውም"
{እንዴት ጠንቋዮች ሚስጥራችንን ሊያውቁ ይችላሉ???}
ከአላህ ሱብሀነሁ ወተአላ በቀር ገይብ( የሩቅ ሚስጥር) የሚያውቅ አለመኖሩ ጥርጥር የለውም እንደው ልባችን እንዲረጋጋ የተወሰኑ የቁርአን አንቀፆች እንመልከት አላህ እንዲህ ይላል" قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلْغَيْبَ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَمَايَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ
«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡ ( አነምል) እንዲሁም በሌላ አንቀፅ እንዲህይለናል عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
«(እርሱ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም።(አልጂን) መልካም ለአብነት ያህል እንዲህ ካልን መጀመርያ ገግይብ ምንድነው? ገይብን በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል:
1ኛ ቋንቋዊ ፍቺው ገይብ ማለት ከሰዎች የራቀ ሁሉ ሲሆን ይህም ክስተቱ ሲከሰት በቦታው አለመገኘት ነገሩን በአንድ ወይም በሌላ መልኩ አለመስማትን ያካትታል።
2ኛ ሸሪዓዊ ፍቺው ነው ገይብ ማለት አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ለነብያቶች በወህይ አማካኝነት የገለፀላቸው ሲሆን ልክ እንደ ጀነት ጀሀነም አሉ ብሎ ማመን መላኢካዎች ጅኖች አሉ ብሎ ማመን ወዘተ ያካትታል። እንዲሁም ገይብ በቀልባችን የቋጠርነው፣ ሚስጥራችንንም ያካትታል።
ታድያ እንዴት ጠንቋዮች ሚስጥራችንን ያውቃሉ ? ነገሩ እንዲህ ነው ማንኛውም ሰው ከተፈጠረ ጀምሮ አብሮት ያለ ቁራኛ (ጅን) አለ። ለዚህም ከቁርአን ማስረጃ ስንመለከት አላህ እንዲህ ይላል" ۞ قَالَ قَرِينُهُۥ رَبَّنَا مَآ أَطْغَيْتُهُۥ وَلَٰكِن كَانَ فِى ضَلَٰلٍۭ بَعِيدٍۢ
ቁራኛው (ሰይጣን) «ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም፡፡ ግን (ራሱ) በሩቅ ስሕተት ውስጥ ነበር» ይላል፡፡( ቃፍ)
ይህ ቁራኛ አብሮን ሁሌም ስላለ እኛ የምናውቀውን ሁሉ ያውቃል በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን አብሮን ስለሆነ ያለፈ ታሪካችን ይሁን አሁን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ከሱ የተሰወረ አይደለም። ጠንቋዮች ደግሞ እንደሚታወቀው ከአላህ መንገድ በመውጣታቸው ምክንያት እንዲሁም ፀያፍና ሽርክያት የሆኑ ነገሮችን በመተገበራች ፣አኼራን ሽጠው ዱየንያን በመግዛታቸው የሚታዘዙዋቸው ጅኖች አሉዋቸው። በመሆኑም አንድ ግለሰብ ጠንቋይ ዘንድ በሚቀርብበት ጊዜ ይህ ከአላህ መንገድ ያፈነገጠው ጠንቋይ ታዛዥ ጅኑን የግለሰቡን ቁራኛ ን( ጅንን) ያለፈ ታሪኩን ወይም ስለ ራሱ እሱ ብቻ የሚያውቀን ሚስጥር እንዲጠይቅለት ያዘዋል የግለሰቡ ቁራኛ ከላይ እንዳሳለፍነው ሙሉ መረጃ ስላለው ለጠንቋዮ ታዛዥ ጅን መረጃ ይነግረዋغል ታዛዥ ጅኑ ደግሞ ለጠንቋዮ እንግዲህ እንዲህ ነው ሚስጥር ሊያውቁ የሚችሉት። በመሆኑም ጠንቋይ ጋር የቀረበው ግለ ሰብ ወደሱ ዘንድ ሲሄድ ያጋጠመውን ፣እኩይ ይሁን ሰናይ ሚስጥሩን ይነገረዋል 'በዚህ ጊዜ ይህ ግለ ሰብ ይደነግጥና ልቡን ይሰጠዋል በሱላይ እምነትም ይኖረዋል። ከዝያማ ከአላህ መንገድ አስወጥቶ ወደ ሽርክ ይመራዋል። ስለዚህ ይህ ጠንቋይ ገይብ አወቀ ማለት ነው? በጭራሽ ከተነገረው ማንም ያውቃል እነዚህ ጠንቋዮች
ህዝባችንን እንዲህ እያታለሉ ከአላህ መንገድ አስወጥተው ዱንያም አኼራውንም አበላሽተዋል። ስለዚህ ወንድም እህቶች ለማያውቁ ወንድምና እህቶች በማሳወቅ ከሽርክ እንዲድኑ ሰበብ እንሁን አበቃሁ ወንድማችሁ abu selim✍
አህሉል አስር አሩቅየቱ ሸርእያ
የቁርኣን ህክምና አገልግሎት መስጫ
አድራሻ አዲስ አበባ እና አካባቢዋ
@ahlulaserarukyeushereiya
@ahlulaserarukyeushereiya
ለበለጠ መረጃ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ማናገር ትችላላችሁ
አቡ ሰሊም 09 13223722
አቡ ሑዘይፋ 09 33189431
በነዚህ አድራሻዎች ብትደውሉ በቂ መረጃ እና አገልግሎት ማግኘት ትችላላችሁ።
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.