ለማንበብ 31 ምክንያቶች
ለምን እናነባለን?
1- ዕውቀትን ለመጨመር እናነባለን፣
2- ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም እናነባለን፣
3- ከድብርት ለመገላገል እናነባለን፣
4- እቤት ቁጭ ብለን ዓለምን ለመዞር እናነባለን፣
5- ለመዝናናት ብለን እንነባለን፣
6- የማስታወስ አቅማችን እንዲዳብር እናነባለን፣
7- ትዝታን ለማምጣት እናነባለን፣
8- ሥራ ላለመፍታት እናነባለን፣
9- ከሥራ ፈቶቸ ለመላቀቅ እናነባለን፣
10- መንፈሳችን እንዲታደስ እናነባለን፣
11- ለመሳቅ እናነባለን፣
12- ለመተከዝና ለመቆዘም እናነባለን፣
13- ከሀሳብ ለማምለጥ እናነባለን፣
14- በሰው ቦታ ሆነን ራሣችንን ለማየት እናነባለን፣
15- ተስፋን ለመሰነቅ እናነባለን፣
16- ባህሪያችንን ለማሻሻል እናነባለን፣
17- አዲስ ነገር ፍለጋ እናነባለን፣
18- የሰዉን እይታና አመለካከት ለማሰስ እናነባለን፣
19- በምናብ ለመዞር እናነባለን፣
20- የራሳችንን ታሪክ ከሌላ ሰው ለመስማት እናነባለን፣
21- ከብቸኝነት ለመውጣት እናነባለን፣
22- ለመነሳሳትና ለመበርታት እናነባለን፣
23- ስህ,ተታችንን ለማረም እናነባለን፣
24- ያነበብነዉን ለማካፈል እናነባለን፣
25- ከእንቶፈንቶ ወሬ ለመራቅ እናነባለን፣
26- ሌሎች እንዲያነቡ ለመገፋፋት እናነባለን፣
27- አዳዲስ ሰዎችንና ሀሳቦችን ለማግኘት እናነባለን፣
28- ያለንበትን ሁኔታ ለመቀየር እናነባለን፣
29- የቀደመዉንና ያለፈዉን ትውልድ ለማነፃፀር እናነባለን፣
30- ለመገረም እናነባለን፣
31- ኢማናችንን ለማሳደግ እናነባለን፡:
@© t.me/sunatube