ስለ ጦርነቱ ውሎ አጫጭር መረጃዎች
፨ እስራኤል ዛሬ እግረኛ ጦሯን ወደ ጋዛ የማስገባት ሙከራ አድርጋ የነበረ ሲሆን ሀማስ ወጥመድ አዘጋጅቶ ጠብቋት የነበረ በመሆኑ ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዳ ጦሯ ወደነበረበት ተመልሷል ። ሀማስ በወሰደው ወጥመዳዊ ጥቃት ሁለት የእስራኤል ቡልዶዘሮችንና አንድ ታንክን ያወደመባት ሲሆን ለጥቃት የመጡ ወታደሮቿንም ገድሏል ። እስራኤል በበኩሏ አንድ ወታደሯ እንደተገደለና 4 የሚሆኑት ደግሞ እንደቆሰሉ ገልፃለች ።
የሀማስ ወጥመዳዊ ጥቃት እስራኤልን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳሰባት ሲገኝ የምድር ጦሯን እንዳታስገባ ካዘገያት ምክንያትም አንዱ ጋዛ ላይ ምን እንደሚጠብቃት ማወቅ አለመቻሏ ነው ።
፨ ሂዝቡሏህ በፈፀመው የሚሳኤል ጥቃት የእስራኤልን የመገናኛና የመረጃ መሰብሰቢያ ራዳሮችን አውድሟል ። እነዚህ የእስራኤል የጦር ተቋማት የሚገኙት ከሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ የነበረ ሲሆን ሂዝቡሏህ የመረጃ አውታሮቹን በሚሳኤል ሲያወድም የሚያሳየውን የቪድዮ ምስልም ለቋል ። ሂዝቡሏህ ከዚህ በተጨማሪም ሁለት የእስራኤል የጦር ጣቢያዎችን መምታቱን አስታውቋል ። እስራኤል ከሂዝቡሏህ በኩል የሚገጥማት ፈተና በእጅጉ የሚከብዳት መሆኑን አልሸሸገችም ።
፨ የእስራኤል ጦር " በስህተት ነው " በተባለ ጥቃት ግብፅ የጦር ላይ ተኩስ ከፍቶ ዘጠኝ የግብፅ ወታደሮችን አቁስሏል ። እስራኤል ጥቃቱ እንደተፈፀመ ወዲያው በስህተት እንደሆነ በመግለፅ ግብፅን ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን ይህ ክስቱት ወደ ጋዛ የሚገባውን የእርዳታ መስመር እንዳይቆርጠው ተሰግቷል ። ግብፅና እስራኤል በዚህ ጦርነት ወደ ግጭት ይገባሉ ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም እንደዚህ አይነት ጥቃቶች ግን አደገኛ መዘዝ እንደማኖራቸው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው ።
፨ አሜሪካ ጦሯ በተጠንቀቅ እንዲቆም አዛለች ። አሜሪካ ጦሯን ያዘዘቺው ወደ ጦርነቱ ኢራን እንደምትገባ በመስጋት ነው ። ኢራን ከገባች እስራኤል ብቻዋን ልትጋፈጣት እንደማትችል የተረዳቺው አሜሪካ ጦሯ ማንኛውንም የኢራን ጦር ጥቃት ለመቀልበስ እንዲዘጋጅ አዛለች ። የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ሊዮድ ኦስቲን ዛሬ የአሜሪካ የአየር መከላከያ ዝግጁ እንዲሆን ያዘዙ ሲሆን ለጦርነት የሚዘምት ጦርም በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዋል ።🇵🇸🇵🇸🇵🇸