Translation is not possible.

ቀኑ የኸንደቅ ዘመቻ ቀን ነበር ...የመካ ሙሽሪኮችና መዲና ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ የተለያዩ የአይሁድ ነገዶች በጋራ በማበር ከ 10,000 በላይ በመሆን ሙስሊሞችን ለማጥፍ መዲናን ከበቧት ..እስልምና አበቃለት  ሙስሊሞችን አጠፏቸው ተባለ ...ረሱሉ ﷺ ለዘመቻው የሚሆን የጦር ምሽግ እየቆፈሩ ሳለ የሮምና ፋርስ ግዛቶች በሙስሊሞች እጅ እንደሚወድቅ ተክቢር እያደረጉ ለባልደረቦቻቸው ነገሯቸው ፡፡ እጠፋለው እያለ የነበረን ባልደረባ ገና የአለምን ኋያላን ታንኮታኩታለህ ሲባል አስቡት ...

ኸንደቅ በድል ተጠናቀቀ ...አመታት አለፉ የረሱሉﷺ ትንቢትም ተረጋገጠ ቂስራና ቀይሰር በሙስሊሞች እጅ ገቡ መንግስታቸውም ተንኮታኮተ ...

:

ጉዳዩ ምን ቢበረታ የፈለገ ቢፈልግ ያበረ ቢያብር ፍልስጤምም ከቆሻሾች እጅ ነፃ ትወጣለች ....

وَنُرِيدُ أَن نَّمُنَّ عَلَى الَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا فِي الْأَرْضِ وَنَجْعَلَهُمْ أَئِمَّةً وَنَجْعَلَهُمُ الْوَارِثِينَ

በእነዚያም በምድር ውስጥ በተጨቆኑ ላይ ልንለግስ፣ መሪዎችም ልናደርጋቸው ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን፡፡ (ቀሶስ 5)

:

ዋናው ጉዳይ ዘመቻው ላይ ያለንን ቦታ መጠየቅ ነው ለጉዙፉ ድል ምን አሻራ ጣልን የሚለው ነው ..

:

ኢማም ዩሱፍ አብደላህ አልቀረዳዊ(ራ ዓ) ለፍልስጤም  አንድ ስንኝ ቋጥረው ነበር  ሱዳናዊያኑም ባማረ ድምፅ አንጎራጉረውታል :–

«انا عائد  اقسمت اني عائد

والحق يشهد لي ونعم الشاهد...»

እመለሳለሁ አዎ እመለሳለሁ

ታሪክ ምስክሬ እውነት ከጎኔ ነው

...

۩۩۩በክብር እንመለሳለን!!! ۩۩۩

📷 የድሉ ቀን በሚል የተሰራ ምናባዊ ምስል...

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group