Translation is not possible.

ሰኞ ማለዳ በእስራኤል እና ሃማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ኃይለኛ እና ገዳይ የሆኑ የእስራኤል የቦምብ ጥቃቶች ተፈፅመዋል።

እስካሁን ድረስ ባለፉት 24 ሰዓታት ቢያንስ 400 ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን ይህ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የህክምና ቡድኖች እና የነፍስ አድን ሰራተኞች ትናንት ማምሻውን የአየር ጥቃቱን ሙሉ ጉዳት ሲገመግሙ መታዘብ ችለዋል።

ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ምን ምን ተፈጠረ፡-

- እስራኤል በጀባሊያ የስደተኞች ካምፕ ላይ በፈፀመችው አንድ የአየር ጥቃት 30 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።

- የእስራኤል ወታደሮች በራማላ፣ ኬብሮን እና ኢያሪኮ አቅራቢያ በርካታ ጥቃቶችን ሲጀምሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በቁጥጥር ስር አዉለዋል፡፡

- የዩኤስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ የምዕራባውያን መሪዎች እስራኤል ለሲቪሎች ከለላ እንድትሰጥ ከማሳሰባቸው በፊት ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት አረጋግጠዋል።

- የጋዛ ሆስፒታሎች ከነዳጅ እና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦት እጥረት በተጨማሪ በርካታ አዳስ ቁስለኞች በየደቂቃዋ ስለሚመጡ ከቁጥጥራቸው ዉጪ ሊሆን እንደሚችል ዕየገለፁ ነው።

- የእስራኤል የአየር ጥቃት በሁለት ሆስፒታሎች አቅራቢያም አል-ሺፋ እና አል-ቁድስ ላይ ደርሷል::

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group