7 month Translate
Translation is not possible.

የወራሪዋ ጦር በታንክና በእግረኛ ወታደር ጋዛን ከቦ ከቆመ እነሆ ቀናቶች ተቆጠረ። "ልገባ ነው እግረኛ ጦሬ ዘመቻ ሊጀምር ነው" በማለት ማስፈራራት ከያዘ ጊዜያት አለፈ።

አሁን ከመሸ የእስራኤል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው እግረኛ ጦሩ ወደ ጋዛ ለመግባት ተዘጋጅቷል ኔታንያሁ ግን ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል ይህ ዘመቻ እንዲዘገይ ፈልጓል ማለቱ ተደምጧል።

ለመሆኑ ከአየር ድብደባ በዘለለ እግረኛ ወታደሮቻቸው ተሰማርተው ፊት ለፊት መዋጋት ለምን ከበዳቸው?!

አዎ ያስፈራል ጥቂት ለአላህ ያደሩ ሙጃሂዶች ለህይወታቸው ቅንጣት የማይሳሱ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የማያውቁ ጦረኞች መሳርያቸውን ሸክፈው በዚክር ታጥረው ይጠብቋቸዋል። ዘመቻውንም "የጀሀነም ሸለቆ" ሲሉ ሰይመውታል። ከወራሪዋ እግረኛ ጦር ጋር ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። ኑ ወደ ጀሐነሙ አርሂቡ በማለት ተንቀሳቃሽ ምስል ለቀዋል። ለመላው የፍልስጤም ህዝብ "መሳሪያችሁን ሸክፋችሁ ለድል አሊያም ለመስዋዕትነት ነፍሳችሁን ሳትሰስቱ ለመስጠት ራሳችሁን አዘጋጁ" በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።

ወራሪዋ በራሷ አንደበት የነፍስ ዋጋ የምንከፍልበት በርካታ ወታደሮቻችን የሚያሳጣ ዘመቻ ቢሆንም እናደርገዋለን እንዘምታለን በማለት በጦር መሪዋ በኩል ተናግራለች።

"ወደ ጋዛ እግረኛ ጦራችንን ማስገባት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ሀማስ ለጥቃታችን ዝግጁ ሆኖ ይጠብቀናል" ማለታቸውም ተደምጧል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group