Translation is not possible.

#አንብቤው_ከተመቸኝ_ላካፍላችሁ!

🔙 ሀዘን እና ትካዜ ወደ ኋላ ጣላቸው!

🌱ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት እንዲህ ይላል፦

✍"ሀዘን ቁርኣን ውስጥ በክልከላ መልኩ ወይም በማራቅ መልኩ ቢኾን እንጂ አልተጠቀሰም

ልክ አላህ እንዳለው

{ وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا }

{አትስነፉ አትዘኑም}

{ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ }

{ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም}"

🔵የዚህ ሁሉ ሚስጥሩ

👉🏽 ሸይጣን ከሚያስደስተው ነገር ሁሉ ትልቁ ሙዕሚን የኾነ ሰው አዝኖ ማየቱ ነው። ከዚያም ከመንገዱና ከጉዞው ሊገታው።

🔵በእርግጥም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሐዘን ተጠብቀዋል

"اللهم إني أعوذ بك من الهم والحزن"

[አላህ ሆይ እኔ ከሀዘንና ከጭንቀት በአንተ እጠበቃለሁ] በማለት

🌱ኢብኑል ቀይም በድጋሚ እንዲህ ይላል፦

✍"ሀዘን ብሎ ማለት

ቀልብን ያደክማል፣ ቆራጥነትን ያከሽፋል፣ ፍላጎትን ይጎዳል፣ ወደ ሸይጣንም ምንም ተወዳጅ ነገር የለም ሙዕሚን አዝኖ እንደ ማየት"

💡ስለኾነም፦

🍎ሀዘንን ራቁ!

   መልካምን ከጅሉ!

      በአላህ ላይ መልካም ግምት ይኑራችሁ!

       አላህ ዘንድ ባለው ተማመኑ

          በአላህም ላይ ተመኩ

              በአላህ ፍቃድ በሁሉም ሁኔታ ደስተኞች ትኾናላችሁ

💡ብትመለከት፦

✍አላህ ብዙ ነገራቶች ሳትጠይቀው ሰጥቶሃል። ስለዚህ አላህ የምትፈልገውን ነገር እንደ ማይከለክልህ እርግጠኛ ሁን። ምን አልባት ግን አለ መሰጠትህ የተሻለልህ ካልኾነ በስተቀር።

🌱ምን አልባት፦

✍አንተ ተኝተህ ሳለህ የሰማይ በሮች ላንተ ዱዐ በሚያደርጉልህ ሰዎች እየተንኳኩልህ ይኾናል።

👉🏽ድሃ ኾኖ የረዳኸው፣

  👉🏽አዝኖ ያስደሰትከው፣

    👉🏽የተጣበበ ኾኖ ያቃለልክለት፣

       👉🏽እያለፈ ብቻ ፈገግ ያልክለት

🤲እጁን ዘርግቶ እየለመነልህ ሊኾን ይችላል።

👇🏾

👉🏽መልካምን ከመስራት መቼም አትቆጠብ

🌱ከቀደምቶች አንዱ እንዲህ ይላል፦

✍"አላህ የኾነ ነገር እጠይቀዋለሁ, ያንን ነገር ከሰጠኝ አንዴ እደሰታለሁ፤  ያንን ነገር ካልሰጠኝ ግን አስር ጊዜ እደሰታለሁ፤ ምክንያቱም መሰጠቴ የእኔ ፍላጎት ነበር አለመሰጠቴ ደግሞ የአላህ ፍላጎት ነው።"

🌱ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይላል፦

✍"ህይወት አጭር ናት።

      👉🏽በሀዘን፣

         👉🏽በጭንቀትና

            👉🏽በጥበት

                👉🏽አታሳጥራት"

🤝በያላችሁበት የአላህ እዝነትና ጥበቃ አይለያችሁ🤲

Send as a message
Share on my page
Share in the group