بسم الله الرحمن الرحيم
👉 ትንሹ ሽርክ
🔑 ይህኛው የሽርክ አይነት እስልምና ወደ ትልቁ ሽርክ ያደርሳል ወይንም ለእርሱ ያጋልጣል ብሎ የከለከለው፤ አላህና መልዕክተኛው ሽርክ ብለው የጠሩት ነገር ግን ከእስልምና እማያስወጣን ተግባር በሙሉ ያካትታል። ምሳሌዎቹም እጅጉኑ የበዙ ከመሆናቸው የተነሳ ለመገደብ ያዳግታል!! ልክ ኢማሙ ኢብኑል ቀዩም " ሽርክ ብዙ አይነት ነው፤ ቁጥሩንም ከአላህ ውጪ ማንም ሊያውቀው አይችልም እንደው እንጠቀስ ብለን ብንጀምር ንግግሩ ከዚህ በላይ በሰፋ ነበር" እንዳሉት ማለት ነው።
👉 ትንሹ ሽርክ ዑለሞች በሁለት መልኩ ይከፍሉታል!!! ይህም ልቦናዊ እና ተግባራዊ ትንሹ ሽርክ በመባል ይካፈላል።
🗝ልቦናዊም የምንለው ሪያዕ፣በሰበቦች ላይ መመካት እና ሌሎችም።
🗝ተግባራዊ እምንለው ደግሞ ከአላህ ውጪ ባለ አካል መማል፣እርዝን ማንጠልጠል( ይህ ተግባር ምንም እንኳን ከቁርዓን የሆኑትን በሚመለከት ኺላፍ ቢኖርም ከብዙ ምክንያቶች አንጻር ግን ቁርዓንም ቢሆን አይቻልም!!!)....በእርግጥም እነዚህ ተግባራት ወደ ትልቁ ሽርክም ሊገቡ ይችላሉ!! ይህ ግን እሚሆነው በባለቤቱ ኒያ ወይም በልቦናው በቋጠረው ነገር ላይ ተመርኩዞ ነው!! ልክ ኢብኑል ቀይም(የኢብኑ ተይሚያህ አንጋፋ ተማሪ መሆኑን ልብ ይሏል) እንደተናገሩት።
👌 ትንሹ ሽርክ ትንሽ ሊባል የቻለው ከትልቁ ማለትም ከእስልምና ሙሉ በሙሉ ከሚያስወጣው አንጻር እንጂ ከሌሎች ወንጀሎች በአጠቃላይ ግን የከፋ ነው!!!
👉 ጠቢቡ ሉቅማን ለአብራኩ ክፍይ
🔅«ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና»
እንዳለውም አላህ ላይ ማጋራት ታላቅ በደል መሆኑ ፍንትው ያለ ሀቅ መሆኑ አይዘነጋም‼️ለዚህም ነው አላህ በተከበረው ቃሉ 🔆"አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡" ብሎ ዛቻ አዘል መልዕክት ያስተላለፈው!! እዚህ ጋር ግን አንድ መነሳት ያለበት ጥያቄ አለ‼️
👌ይህ ዛቻ ትንሹን ሽርክም ያካትታል ወይንስ ትልቁን ሽርክ ብቻ ነው⁉️⁉️
መልስ
🔑 በእርግጥ ዑለሞች በዚህ ርዕስ የተለያየ እይታ አላቸው። ታላቁ ዓሊም መጽሐፉ ግመል ከምትሸከመው በላይ የበዙ፣ ህይወቱን በሙሉ ለእስልምና የሰዋ የእስላምና ጀምበር!! የሆነው ኢብኑ ተይሚያህ( ገና በአስራዎቹ ዕድሜው ነበር ኪታቦችን መጻፍ የጀመረው!!) እራሱ ሁለት አይነት ንግግር አለው!! ይህም:-
1ኛው- ሽርክን አላህ አይምርም ትንሹም እንኳ ቢሆን
2ኛው- ያ አላህ እማይምረው እሚባለው ሽርክ ትልቁ ሽርክ ነው!! የሚል ነው። ነገር ግን ከተለያዩ አቅጣጫዎች አስረድተው ሸይኽ ዑሰይሚን ቀውሉል ሙፊድ በተሰኘውና በሌሎች መጽሀፎቻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሁሉንም ያካትታል ወደሚል ድምዳሜ ያዘነብላሉ። ትንሹ ሽርክ ከባድ ከመሆኑ የተነሳም ነው ዐብደላህ ኢብን ዑመር ከአላህ ውጪ ባለ አካል በእውነት ከምምል በእውሸት በአላህ ብምል ይሻለኛል ያሉት!! አስተውሉ‼️ ትንሹን ሽርክ ያስገኘ እሳት ይዘወትራል ወይንም ከእስልምና ይወጣል ማለት ሳይሆን በወንጀሉ ልክ ተቀጥቶ ከእሳት ይወጣል!!! ሌሎች ከሽርክ ውጭ ያሉ ወንጀሎችን ግን አላህ ከፈለገ ይምረዋል ወይንም በወንጀሉ ልክ ይቀጣዋል!!
👉 እጅጉኑ ልብ በሚያደማ መልኩ ይህ ሽርክ ሁል ጊዜ መልኩን እየለዋወጠ ወደ ሙስሊሙ ዑማ ሰርጎ ከመግባት አልቦዘነም!! ለዚህም ሁላችንም እምናውቃቸው ብዙ ምሳሌዎች አሉ። አዎን ሽርክን ወደ እስልምና ለማስገባት የእስልምና ጠላቶች በኛው ቂላቂል ጥቅመኞች በኩል ያላሰለሰ ጥረቶችን ሲያደርጉ ይስተዋላል። ለዚህም በየ አከባቢው ያሉ ዶሪሆች፣ በየግዜው እስላማዊ ተብለው እሚለቀቁ የሽርክ ሙዚቃዎች(አስቡት!! አንድ ሙስሊም ይህንን እያደመጠ እና እየጨፈረበት ቢሞትና አላህን ቢገናኝ መልሱ ምን ይሆን????!!!!) እና ሌሎችም ተግባራት ታላቅ አስረጂ ናቸው!!! ይበልጡኑ ሽርክ ምን ያህል እስልምና ውስጥ ሰርጎ እንደገባ ግልፅ ይሆንልን ዘንድ ሸይኽ ፈውዛን ኢርሻድ በተሰኘው መፅሓፋቸው ያሰፈሩትን በአንድ ሙስሊም ቀብር አምላኪና ጣዎት አምላኪ መካከል የተከሰተውን ምልልስ እንመልከት⤵️⤵️
🔆 አንድ ቀብር አምላኪ አንድን ጣውት አምላኪ አገኘውና 'አንተ ሰውዬ እንዴት ይህን ግዑዝ አካል ታመልካለህ' ብሎ በመተቸት መንፈስ ጠየቀው!!
🔆ጣውት አምላኪውም የዋዛ አልነበረምና 'እኔስ በእጄ ያለን ግዑዝ አካል ነው እማመልከው አንተ ግን በእጅህ(በአቅራቢያህ) የሌለን ግዑዝ አካል(ቀብርን)ን እኮነው የምታመልከው' ብሎ መለሰለት ይባላል!!!! ልብ ይበሉ! ምንም እንኳን ሁለቱም አካላት ሽርክ ላይ ቢወድቁም የእስልምናን ካባ ለብሶ ያለ አካል የባሰ የሽርክ አረንቋ ውስጥ እንዳለ ልብ ይሏል!! ታድያ እኛም ሆንን በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ከዚህ አደጋ ጠርተናልን⁉️⁉️
👉 እናም ይህን ታላቅ በደል ለራሳችን ሙሉ በሙሉ ርቀን ለማህበረሰባችን የማስተማር ግዴታ ተጥሎብናልና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል ልናስተምራቸው ይገባል!!
አላህ ሆይ እኛንም ሆነ መላውን ሙስሊም ከሽረክ ጠብቀን‼️ ዳዒዎቻችንም ከሽርክ በማስጠንቀቅ ላይ አጽናቸው‼️ አንተ የባሪያዎችህን ጥሪ ሰሚ ነህና🤲🤲🤲🤲
والله أعلم والعلم عنده
✍አቡ ረምዛን
for more follow 👉https://ummalife.com/aburemzan
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.