7 month Translate
Translation is not possible.

ሱኒዩ ማኅበረሰብ ሊነቃ ይገባል‼️

=========================

"መልዕክቱን ለሚመለከተው ሁሉ አድርሱልኝ።"

||

✍️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአሕባሽ፣ የሱፍያ፣ የተብሊጝና መሰሎቻቸው ርዕዮት አራመጅ የሆኑ ቡድኖች አንድ ላይ ተናበው እየሠሩ ነው።

በተለያዩ ስያሜዎች ማህበሮችን በማቋቋም እየተደራጁ ነው።

ለአብነት ያክል፤

✔️ የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር፤

✔️ የአዲስ አበባ ኢማሞች ማኅበር፣

✔️ የአዲስ አበባ ሙስሊም ሴቶች ማኅበር፣

.

.

.

ወዘተ የመሣሠሉት ይገኙበታል።

እነዚህ ማኅበራት ስያሜያቸው ከላይ ሲታይ ሁሉን አቀፍ ይመስላል እንጅ ሁሉም የአሻዒርዮች ናቸው።

ለምሳሌ፦ የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር ማለት ባለፈ ሚሊኒዬም አዳራሽ የመውሊድ ዝግጅት በግንባር ቀደም ተዋናኝነት ያዘጋጀው ነው።

ምናልባትም ይህ መደራጀታቸው፤

ወደፊት ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የመጅሊስ ምርጫ ሂደት፤

የተቃናና ውጤታማ የምርጫ ቅስቀሳ ለማስኬድ ታስቦ ይሆናል።

ስለዚህ ሱኒዩ ማኅበረሰብ ሊነቃ ግድ ይለዋል።

እርሱም በተለያዩ ዘርፎች ሊደራጅና ራሱን ከታች እስከ ላይ ሊያዋቅር ይገባል።

እነዚህ ማኅበሮቻቸው ህገ-ወጥ እንዳይሆኑ፤

ማኅተሙ በእጃቸው ስላለ ህጋዊ አድርገዋቸዋል።

ማፍረስም አይቻልም።

የሚያዋጣው ለራስ መደራጀት ነው።

እነዚህ ሰዎች ኋላ ተደራጅተው ከጨረሱና አማራጭ ካገኙ፤

ዛሬ ላይ የሚዘምሩልህን የውሸት አንድነት ይክዱሀል።

ለራሳቸው ከተመቻቸው ብትለምናቸው ራሱ ዙረው አያዩህም፣ አይሰሙህም። ከወዲሁ ንቃ።

ቢያንስ አንተም ከተደራጀህ ግን ሳይወዱ በግድ አንድ ይሆናሉ፤ አሊያም ይበተናሉ።

*

በፊት ሁላችንም የተቃወምነው አሕባሽን ነበር።

ዛሬ ግን አሕባሽ ከሱፍያው ጋር ተጨፍልቃ፤

አመለካከቷን ያለምንም ተቃርኖ ደህና በነጻነት እያስተላለፈችና አድማሷን እየዘረጋች ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

እንዳውም ከበፊቱ ይልቅ ዛሬ ላይ አሕባሾች ክንፋቸውን እየዘረጉ ነው።

ስለዚህ መንቃት ግድ ነው ወዳጄ!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group