ለእስራኤል ፖሊስ መለዮ ያቀርብ የነበረው ኩባንያ ውሉን አቋረጠ
የህንዱ ማርያን የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ለእስራኤል ፖሊስ መለዮ በማቅረብ ላይ ነበር
አል-ዐይን
2023/10/21 12:59 GMT
ኩባንያው ውሉን ያቆመው የእስራኤል ፖሊስ የስነ ምግባር ጥሰት ፈጽሟል በሚል ነው
ለእስራኤል ፖሊስ ዩኒፎርም ያቀርብ የነበረው ኩባንያ ውሉን አቋረጠ።
የእስራኤል-ሀማስ/ፍልስጤም ጦርነት ከተጀመረ ሁለት ሳምንት ያለፈው ሲሆን እስካሁን ከስድስት ሺህ በላይ ዜጎች ከሁለቱም ወገን ተገድለዋል።
የዓለምን ትኩረት የሳበው ይህ ጦርነት ከብዙ ጉዳዮች ጋር የተገናኘ ሲሆን ለእስራኤል ፖሊስ አባላት መለዮ ሲያቀርብ የነበረው ኩባንያ ውሌን አቋርጫለሁ ብሏል።
የህንዱ ማርያን ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ለእስራኤል ፖሊስ መለዮ በማቅረብ ላይ የነበረ ሲሆን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ውሉን ማቋረጡን አስታውቋል።
ኩባንያው ውሉን ያቋረጠው የእስራኤል ፖሊስ የሙያ ስነ ምግባሩን ጠብቆ እየሰራ አይደለም በሚል እንደሆነ ኢንዲያን ታየምስ ዘግቧል።
የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ቶማስ አሊካል እንዳሉት የእስራኤል ጦር በተለይም በጋዛ በሚገኘው አል አህሊ ሆስፒታል ላይ የፈጸመው ጥቃት ውሉን እንዲያቆም ዋነኛው ምክንያት ነው።
በመሆኑም እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰላም እስኪያወርዱ ድረስም አዲስ ትዕዛዝ ከእስራኤል ፖሊስ እንደማይቀበል ኩባንያው ገልጿል።
ይሁንና ከዚህ በፊት የእስራኤል ፖሊስ ከኩባንያው ጋር የገባቸውን ስምምነቶች እንደሚያከብር ተጠቅሷል።
የእስራኤል ጦር ጥቃት ሀማስን ኢላማ ያደረገ ነው ቢባልም ንጹሀን ዜጎች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል ተብሏል።
አሜሪካ በቀጥታ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ላይ ስትሆን የእስራኤልን ድርጊት በርካቶች ራስን ከመከላከል ያለፈ እንደሆነ እየገለጹ ይገኛሉ።
ጦርነቱ በሚቆምበት ሁኔታ እና ለፍልስጤማዊያን ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ያለመ ውይይት በግብፅ አስተናግጅነት የበርካታ ሀገራት መሪዎች ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።