Translation is not possible.
በለንደን በተካሄደ የፍልስጤም ድጋፍ ሰልፍ 100ሺ ሰዎች መሳተፋቸው ተገለጸ
 
የአረብ ሀገራት እስራኤል ተኩስ እንድታቆም ያደረጉት ጥረትም አልተሳካም
 
ቀዳሚ ገፅ
 
ዜና
 
አስተያየት
 
ፖለቲካ
 
ኢኮኖሚ
 
ማህበራዊ
 
ልዩልዩ
 
ስፖርት
 
የመረጃ ሳጥን
 
ተመልከት
 
ፖለቲካ
 
በለንደን በተካሄደ የፍልስጤም ድጋፍ ሰልፍ 100ሺ ሰዎች መሳተፋቸው ተገለጸ
 
የአረብ ሀገራት እስራኤል ተኩስ እንድታቆም ያደረጉት ጥረትም አልተሳካም
 
አል-ዐይን
 
 2023/10/22 8:19 GMT
 
ሰልፈኞቹ በዳውኒንግ ጎዳና ከመሰባሰባቸው በፊት "ነጻ ፍልስጤም" የሚል መፈክር ከፍ አድርገው አሰምተዋል
በእንግሊዝ ለንደን ከተማ በተካሄድ የፍልስጤም የድጋፍ ሰልፍ ላይ ወደ 100ሺ የሚጠጉ ሰልፈኞች ተሳትፈዋል።l
ሰልፈኞቹ እስራኤል ሀማስ የሰነዘረባትን ጥቃት ተከትሎ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
 
ሰልፈኞቹ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ መኖሪያ በሆነው በዳውኒንግ ጎዳና ከመሰባሰባቸው በፊት "ነጻ ፍልስጤም" የሚል መፈክር ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
'በፍልስጤም አጋርነት ዘመቻ' በተጠራው ሰልፍ 100ሺ ሰዎች መሳተፋቸውን ፖሊስ ግምቱን አስቀምጧል።
 በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በተለይም በሙስሊም ሀገራት ቁጣ ተቀስቅሷል፣ የአጋርነት ሰልፎችም ተካሂደዋል።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በጥብቅ የሚጠበቀውን የእስራኤል ድንበር ጥሶ በመግባት ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል እየወሰደች ያለችውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።
ሀማስ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት የምትለው እስራኤል 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች እንዲወጡ ማስጠንቀቋም ይታወሳል።
እስራኤል ከአየር ድብደባ ጎን ለጎን ጋዛን በእግረኛ ወታደር ለማጥቃት በድንበር አካባቢ ወታደሮቿን አከማችታለች።
የአረብ ሀገራት እስራኤል ተኩስ እንድታቆም ያደረጉት ጥረትም አልተሳከም።
ምዕራባውያንም ቢሆን ስለተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ እንጂ የተኩስ መቆም ጉዳይ አላስጨነቃቸውም።ሰልፈኞቹ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ መኖሪያ በሆነው በዳውኒንግ ጎዳና ከመሰባሰባቸው በፊት "ነጻ ፍልስጤም" የሚል መፈክር ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
ሰልፈኞቹ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ መኖሪያ በሆነው በዳውኒንግ ጎዳና ከመሰባሰባቸው በፊት "ነጻ ፍልስጤም" የሚል መፈክር ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group