ወሬን በምሳሌ ውሃን በብርሌ እንደሚለው የሃገራችን ሰው ያማረ ንግግር በሚያምር ተናጋሪ አዱኒያን በምሳሌ ሲያስቀምጥልን እንድህ ይለናል።
💞"የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶቿ (የአዱኒያ ሰዎች) በርሷ ላይ እነርሱ( ሁሉንም ነገር) ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ናት፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን።💞"
በሌላ አንቀጽ
💞 "ለእነሱም የቅርቢቱን ሕይወት ምሳሌ አውሳላቸው፡፡ (እርሷ) ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር በቃይ እንደ ተቀላቀለበት (ከተዋበ በኋላ ደርቆ) ነፋሶችም የሚበትኑት ደቃቅ እንደ ኾነ ብጤ ናት፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ "💞
በሌላም ቦታ እንድሁ"
💞"የቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት። በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም
ምሕረትና ውዴታ አልለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡"💞
የእሷን እርባና ቢስነት አንቆርቁሮ ጉሮሮ በሚሰርቀው መልኩ ከገለጸልን በኋላ በዚች አለም ጥፍጥና እንዳንታለል ለበለጠ ነገር አሻግሮ ሲያስከጅለን በመደምደሚያው እንድህ ይለናል ።
💞"ከጌታችሁ ወደ ኾነች ምሕረት፣ስፋቷ እንደ ሰማይና ምድር ስፋት ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፡፡ ለእነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች፡፡ ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡" 💞 ምን ያማረ ንግግር ባማረ ተናጋሪ !! ለዚች ሃገር ምን ያስፈልጋት ይሆን? የሁላችንንም መልስ የሚሻ ነው ባረከሏሁ ፊኩም!