Tarjima qilib boʻlmadi.

በፍልስጤሟ ምድር ጋዛ ወራሪዋ እስራኤል ከሰማይ የወረወረችው የድሮን ቦንብ ቤታቸው ዶግ አመድ አድርጎ ላያቸው ላይ ተናደ። አስራ አንድ ሙሉ ቤተሰብ ከፍርስራሹ መሐል ተጋደመ። ቦታው ላይ የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቆፍረውና ቧጠው ሲያወጧቸው ሁሉም ሞተው እናት ነፍሷ ከጀሰዷ ሊላቀቅ የመጨረሻ እስትንፋሷ ላይ ነበረች።

በዝግታ አይኗን እያስለመለመች ታቃስታለች። በሆዷ የታቀፈችው ፅንስ በህይወት ይቆይ ዘንድ እግሯን ከፈት ልጇን ደገፍ አድርጋ ተንጋላለች። ሆስፒታል እንደደረሰች እስትንፋሷ ተቋርጦ ጌታዋን ስትገናኝ ፅንሱ ግን በህይወት ነበር። ዶክተሮች በአላህ ፈቃድ የልጁን ህይወት ማትረፍ ቻሉ። አስራ አንድ ሙሉ ቤተሰቦቹን ባጣበት ቅፅበት እርሱ ይህቺን አለም ተቀላቀለ። መገን የአላህ ስራ ጉድ ነው የእሱስ አቻቻል።

Mahi mahisho

https://ummalife.com/mahimahisho

image
Xabar sifatida yuborish
Sahifamda baham ko'rish
Guruhda ulashish