Translation is not possible.

☑️ ከሚስቱ ጋር ጉዞ ለሚወጣ…

★★

📍ኢማም ኢብኑልቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

«ያገባ ሰው ከባለቤቱ ጋር ጉዞ ከወጣና የሆነ ቦታ መኖር ከጀመረ ሶላቱን አያሳጥርም። ምክንያቱም ሴት ልጅ ሀገር እንዲሁም መኖሪያ ነች። የትም ከተገኘች መረጋጋትንም ይገኛል።»

📍አብደላህ ኢብኑ አባስ አላህ መልካም ስራው ይውደድለት እንዲህ ብሏል።

«መንገደኛ ሰው ካገባ ሶላቱን መሙላት ግድ ይለዋል።»

📚زاد المعاد  [ 453/1]

📍ሸኽ መሀመደል አሚን አሽንዊጢይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

«ሙሳፊረ የሆነ ሰው የሆነ ሀገር ላይ ካገባ ወይም ሚስቱ ባለችበት ሀገር የሚያልፍ ከሆነ ሶላቱን አሟልቶ ይሰግዳል። ምክንያቱም ሚስት የሀገር ፍርድ ትይዛለች። ይህ የኢማሙ ማሊክ፣ የአቡ ሀኒፋ የጓደኞቹና የኢማሙ አህመድ አቋም ነው። ኢብኑ አባስም ይህን ብሏል።»

📚 أضواء البيان [1/278]

Send as a message
Share on my page
Share in the group