Translation is not possible.

بسم الله الرحمن الرحيم

የሰው ልጆች የተፈጠሩበትን አላማ አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ሲል ይነግረናል፣ الذاريات

((وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ))

"ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡"

በዚህም እኛ ሰዎች የተፈጠርንበት ብቸኛ አላማ አላህን በብቸኝነት ለማምለክ እንደሆነ እንረዳለን እንድሁም ዱኒያን ማከማቸት እና ለዱኒያ መኖር እኛ ሰዎች የተፈጠርንበት አላማ እንዳልሆነ እንረዳለን!! በዚህም የተፈጠረበትን አላማ ያሳካ የሆነ ለተፈጠረለት አላማ ኖሮ ዱኒያን ችላ ብሎ ጌታውን የተገናኘ ሰው ቀኑ ደርሶ ጠፊ የሆነችውን ዱኒያ ሲሰናበት ማረፈያው ጀነት ትሆናለች!! የተፈጠረለትን አላማ ዘንግቶ ጠፊ በሆነችው በዱኒያ ብልጭልጭ ተሸውዶ ጌታውን ችላ ያለ ሰው ደግሞ ቀኑ ደርሶ ዱኒያ ላይ ያከማቸውን የዱኒያ ብልጭልጭ ጥሎ በሚሞት ጊዜ ይህ ሰው መኖሪያው ጀሐነም ይሆናል ማለት ነው!!

👉👉👉👉የጀሐነም መገለጫዎች

👉## የጀሐነም እሳት ቃጠሎዋ በጣም አደገኛ ነው እኛ እዚህ ዱኒያ ላይ የምናውቀው እሳት ከጀሐነም እሳት ሰባኛው ክፍሏ እንደሆነ በሀድስ ተነግሯል!! ጌታችን አላህም እንድህ ይላል፣

((وَكَفَى بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا))

"አቃጣይነትም በገሀነም በቃ፡፡" ሱራ አን-ኒሳእ-55

👉## የጀሐነም ምግብ ዘቁም የሚባል ዛፍ ሲሆን ይሄም ዛፍ ጣእሙ ይቅርና መልኩ ራሱ ለማየት የሚያስጠላ የሆነ

((لَّا يُسْمِنُ وَلَا يُغْنِي مِن جُوعٍ))

"የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡" ሱራ አልጋሲያህ-7

((إِنَّ شَجَرَتَ الزَّقُّومِ، طَعَامُ الْأَثِيمِ، كَالْمُهْلِ يَغْلِي فِي الْبُطُونِ ، كَغَلْيِ الْحَمِيمِ))

የዘቁመ ዛፍ፣የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡ እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡ ሱራ አድ-ዱኻን 43-46

ከዚህ ዛፍ ጠብታ የዱኒያ ምድር ላይ ጠብ ብላ ብታርፍ የምድር ሰዎችን ኑሮ ባበላሸችባቸው ነበር ተብሏል በሀድስ!! ይህ ከመሆኑ ጋር ግን የጀሐነም ሰዎች ምግብ ይህ አስቀያሚ ዛፍ ነው!!

👉## የጀሐነም መጠጥ በሙቀቱ ብርታት ድካ የደረሰ የፈላ ውሃ እና የእሳት ሰዎች እዥ ሲሆን፣

((يُصَبُّ مِن فَوْقِ رُءُوسِهِمُ الْحَمِيمُ)) ((يُصْهَرُ بِهِ مَا فِي بُطُونِهِمْ وَالْجُلُودُ))

"ከራሶቻቸው በላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧቸዋል:: በሆዶቻቸው ውስጥ ያሉ ቆዳዎቻቸውም በእርሱ ይቀለጣሉ፡፡" ሱራ አልሃጅ 19-20

👉## የቅጣቷ ክፋት የሰው ልጅ ሲስማው እንኳ ጤነኛ ኡእምሮ ካለው በርግጎ ወደጌታው እንድዋደቅ ያደርጋል።

((إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَاهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا الْعَذَابَ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمًا))

እነዚያን በተአምራታችን የካዱትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን፡፡ ስቃይን እንዲቀምሱ ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ አን-ኒሳእ-56

እንግድህ የጀሐነም ቅጣት እንድህ ነው ቆዳዎች በቃጠሎው እርር እንኩትኩት ባለ ቁጥር ሌላ ቆዳ ይቀየርላቸዋል ይህም የቅጣቱን አስከፊነት እንዲቀምሱ ነው!!

አላህ እኔንም ሙስሊሞችንም ከዚች አስከፊ ጀሐነም ይጠብቀን!! አሚን

6 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group