•ከአመታት በፊት አንድ የሙስሊም ሀገር ላይ አንድ ሼኽ በሆነ መንደር ሲያልፉ የተወሰኑ ወጣቶች ቁማርና መሰል ሀራም ነገሮችን ሲፈፅሙ ይመለከቱና መጥፎ ነገር ሲሰራ ያየ በእጁ ይከላከል የሚለውን ሀዲስ ተግባራዊ ለማድረግ ሂደው የሚጫወቱበትን ብትንትን አድርገው አላህን እንዲፈሩና ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ተቆጥተው ይናገሯቸዋል።
ሼኹ በፈፀሙት ተግባር ስሜታቸውን መቆጣጠር ያቃታቸው ወጣቶች ሼኽዬውን ይደበድቧቸዋና እንሱ ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ።
•በሌላ ቀን ሌላ ሼኽ በዚሁ መንደር በነዚህ ወጣቶች መሀል ያሀንኑ ሀራም ተግባር እየፈፀሙ ያልፋሉ።
እኚ ሼኽ መጥፎ ነገር ሲሰራ ያየ በእጁ ይከላከል የሚለውን ሀዲስ የተረዱበት መንገድ ከመጀመሪያው ፍፁም ይለያይ ነበር፣በመጀመሪያ ሄደው ለነዚህ ወጣቶች ከጥሩ ፈገግታ ጋ ኢስላማዊ ሰላምታን ያቀርቡላቸውና ያልፋሉ በሌላ ቀን ከሰላምታው በተጨማሪ በእጃቸው የሆነች ፍራፍሬ ነገር ይዘው ይመጡና ለሁሉም ይሰጧቸዋል፤በዚህ መልኩ የወጣቶቹን ልብ መግዛት የቻሉት እኚህ ሼኽ በሌላ ቀን መስጂድ የሆነ ፕሮጋራም እንዳለና ለመሄድ ፍቃደኛ ከሆኑ ይጠይቋቸዋል ብዙም ሳያንገራግሩ እሺ ብለው ይሄዳሉ፤መጠጥ ቤትና መሰል ሀራም ቦታዎች ይሄድ የነበረው እግራቸው አላህ እኚህን ሼኽ ሰበብ ያደርግላቸውና ወደ መስጂድ ይመላለስ ጀመር እነዚህ ሸባቦች በጊዜ ሂደት ተለውጠው የመስጂድ ሰው ለመሆን በቁ።ሀዲሱን በጥሬው ተረድተው ሂክማ ያነሳቸው(ደብድበዋቸው) የነበሩትን ሼኽ ሂደው አውፍ እንዲሏቸው ይጠይቃሉ።
~~~~~~~~~~~~~