UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ማሊ ወሊዱኒያ 🙄🙄

6 month Translate
Translation is not possible.

እንዴት አደራችሁ 😊😊

ሁሌም ቢሆን ሳስበው ሚያስገርመኝ ነገር አለ... ያ አስገራሚ ነገር ምንድነው ካልችሁኝ እንግዲህ ልንገራችሁ 😊😊...

ታላቁ ጌታችን አላህ ተባረከ ወተዓላ ሰላት ስገዱ ብሎ ግዴታ ሲያደርግብን እኛን ብቻ ነው ያዘዘው...ዘካ አውጡ ሲለንም እኛኑ ብቻ ነው ያዘዘው...ሃጅ አድርጉ ሲለንም እኛኑ ብቻ ነው... መልካምን አድርጉ የተባለውም እኛን ነው... ነገር ግን ተቆጥሮ ከማያልቀው ወደ አላህ መቃረብያ ነገሮች መካከል አንዱ በጣም ያስገርመኛል... ይሄን አስገራሚ መልካም ሥራ አላህ ራሱ አድርጎታል... መላይካዎችም አድርገውታል... ከዛ እኛ ታዘናል ♥️♥️

አላህ እና የርሱ ታዛዥ መልአኮች በነብዩ ላይ ሰለዋትን ሚያወርዱ ከሆነ እና አውርዱ ተብለን ከታዘዝን ምንድነው ምንጠብቀው 🙄🙄

ሃያ የበዛ ሰለዋትን እናውርድ 😊😊

የተባረከ ጁሙአ ይሁንልን ♥️♥️

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

አንዳንዴ ከትንሽዬ ልብህ በላይ የሆነ ትልቅ ነገር ማሰብ ትጀምራለህ... ትደነግጣለህ ምክንያቱም ልብህ ትንሽ ናት የጀመርከውን ሃሳብ መጨረስ አለመጨረስህን እንኩዋን አታውቅም...

ምናልባትም በመሃል ልብህን ልታጣው ትችላለህ 🙄🙄

ምናልባትም በአካል ልትደክም ትችላለህ 🙄🙄

ምናልባትም እጅ ልትሰጥ ትችላለህ 🙄🙄

ምናልባትም ሕይወትህን ልትሰጥ ትችላለህ 🙄🙄

ግን ትልቁ እና አስፈላጊው ነገር በዚ ሃሳብ ምክንያት የሚመጣውን ችግር እና ናፍቆት ድካም እና ማጣት በትግስት ችለህ መቆየት ነው... ምክንያቱም ይሄ ሃሳብ ሕይወትህን ሊያሳጣህ ቢችልም ሕይወትህን ሕይወት ያደረገውም ይሄው ራሱ ሃሳብ ነውና... ምንድነው ይሄ ሃሳብ... ምንድነው ይሄ ጭንቀት... ምንድነው ይሄ ጉዳይ...ሌላ ሊሆን አይችልም የአለማቱ ጌጥ የልባችን ናፍቆት የሁልጊዜ ጀግናችን የሰው ልጆች አለቃ የሆኑት የአዛኙ ጌታ እዝነት የፍጥረተ አለሙ ክስተት የዘመናት ተአምር የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይህ ወሰለም ፍቅር ነው ♥️♥️♥️

ስለርሳቸው ፍቅር ማሰብ,መፃፍ, ማስታወስ ሁሌም መጨነቅ ይገባናል 😍😍😍

እናንተስ

ምን ትላላችሁ??👇👇

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

አንቱን ለማሞገስ ቢታገል በከንቱ,

ብዕሬ ከበረ አንቱን በመጥራቱ,

ግጥሜም ተዋበ ስምሆን በማውሳቱ,

አንቱን በማለቱ...

ሰለላሁ አለይህ ወሰለም ♥️♥️

✍ Mahi z

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

አንዳንድ ትንንሽ ወንጀሎችን ስንዳፈር ሌሎች ወንጀሎችን እንድንሰራ በር ይከፍታል።ለዛ ነው <አላህ የከለከለውን ሙሉ ለሙሉ አታድርጉ ያዘዘውን ደግሞ የቻላቹትን ያህል ስሩ> የተባልነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

ጠንከር ማለት አይሻልም ወይ?? 🙄

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group