UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Followers
1
abu mahir shared a
Translation is not possible.

ዱኒያ... የፈተናዎች አዳራሽ!

በዚህች ምድር ላይ ሲኖር የማይፈተን ማንም የለውም። ልዩነቱ ያለው የፈተናው ዓይነትና ብዛት ላይ ብቻ ነው።

በተለያየ መልኩ ልንፈተን እንደምንችል አላህ   سبحانه وتعالى ምሎ ነግሮናል

▪በፈተና ጊዜ የማይታገሱን አውግዟል የጌታቸውን ውሳኔ ወደው የሚቀበሉና የሚታገሱትን አወድሷል በዚህች ምድርም መጨረሻቸው እንደሚያምርና በቀጣዩ ዓለም ህይወታቸውም እጥፍ ድርብ ምንዳ እንደሚለግሳቸው ቃል ገብቷል።

💥እንደሚፈተኑና ፈተናዎች ውስጥ መሆንን አለማወቅ እራሱ አንድ ፈተና ነው።

▪ከፈተናዎች ሁሉ ከባዱ ፈተና ደግሞ ዋና ሃብታችን የሆነው እምነታችንን(ዲናችንን) የሚጎዳ ፈተና ነው።

ከዚህ ውጭ ያሉ ፈተናዎችን በሙሉ በአላህ እገዛ ተቋቁሞ ማለፍ ይቻላል ቢወድቁና ቢሰናከሉም ዳግም የመነሳት እድል ይኖራል ምክንያቱም የዲን ገመዱ ጠንካራ የሆነ ሰው ወድቆ አይቀርምና ነው!

▪ሌሎች ፈተናዎች ሲበዙብን ወደ አላህ በመሸሽ የዲን/የኢማን ምሽግ ውስጥ በመግባት መዳን እንችላለን

ዲናችንን የሚያደክም ፈተና ከበዛ ግን መሸሻ

እናጣለን ለዚህም ነው ፥

( ولا تجعل مصيبتنا في ديننا)

"አላህ ሆይ፥ የሚደርስብንን ችግር ዲናችን ላይ ያነጣጠረ አታድርግብን" የሚለው ዱዓ ከተመረጡ ዱዓዎች መካከል አንዱ የሆነው።

ህመም፣ድህነትና ረሃብ ወዳጅን በሞት ማጣትና የህይወት አለመረጋጋት ወዘተ ዱኒያ ላይ ሊገጥሙን የሚችሉ *ፈተናዎች* ናቸው

▪ማጣት ብቻ ሳይሆን ማግኘትም ፈተና ነው!

▪መታመም ብቻ ሳይሆን ሁሌ ጤነኛ መሆንም ፈተና ነው!

▪አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን ማወቅም ፈተና ነው

በጥቅሉ፥ ዱኒያ ላይ ያለ ነገር በሙሉ ፈታኝ ነው ማለት ይቻላል!

ለዚህም ነው ጌታችን አላህ፥

(إِنَّا جَعَلْنَا مَا عَلَى الْأَرْضِ زِينَةً لَهَا لِنَبْلُوَهُمْ أَيُّهُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا)[سورة الكهف 7]  ያለው

ሁሉም የሰው ልጅ  የፈተና ድርሻ እንዳለው አውቆ ማደርና ተራችን ሲደርስም በትዕግስትና አላህን በመመካት ከችግሮች ለመውጣት መጣር ተገቢ ነው።

اللهم لا تجعل مصيبتنا في ديننا

ولا تجعل الدنيا أكبر همنا ولا مبلغ علمنا ولا إلى النار مصيرنا

واغفر اللهم لنا ولوالدينا

ومن خزي الدنيا وعذاب الآخرة أجرنا

✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ረጀብ20/1440ዓ.ሂ@ዛዱል መዓድ

https://t.me/zeyneseid

🔸  🔹  🔸  🔹  🔸

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abu mahir Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group