💎የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው፣ አይበድለውም፣ ለጠላት አሳልፎም አይሰጠውም።»
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።
«ወንድሞቼ ሆይ! አላህን ፍሩ፣ ለራሳችሁም መልካም አድርጉ፣ አላህ ያዘዘውን የእምነት ወንድማማችነት አሳኩ፣ እውነት የተናገረን፤ እውነት ተናግራሃል ፣
አበጀህ በሉት፣ መልካሙን ጠቁሙት፣ አመስግኑት አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጉለት።
ጥፋተኛውን፣ “ልክ አይደለህም፣ ተሳስተሃል” በማለት በእርጋታ እና በጥበብ ንገሩት። አቅጣጫም ስጡት ምከሩትም። በዚህም የተነሳ ጥራት ይገባውና ከአላህ ታላቅ ሽልማት፣ ከሰዎች መልካም ውዳሴ እና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር መልካም ስም ታተርፋላችሁ። ከመጥፎ ዝንባሌ እና አክራሪነት፣ እንዲሁም ከጨለምተኝነት ተጠንቀቁ። አትራፊ ትሆናላችሁ፣ ጥሩውን ውጤት ታገኛላችሁ።”
📕መጅሙዕ አልፈታዋ (4/165)