umma1698436995 Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ጋዛ ሙሉ በሙሉ በጨለማ ተውጣለች ። ኢንተርኔት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል ። ጋዛ ከአለም ሁሉ ተነጥላለች ።

በጨለማ ውስጥ ያለቺውን ጋዛን የሚያፈጋት ከአሜሪካ ሰራሽ የጦር ጄቶች የሚወረወረው የእስራኤል ሚሳኤል ብቻ ነው ።

ሆስፒታሎች ስለወደሙ ስራ አቁመዋል ። ውሀ መብራት ነዳጅ ሁሉም እዚያ የለም !

እዚያ ያለው የአላህን እርዳታ በመጠባበቅ የሚታገሉ ፍልስጤማዊያን ብቻ ናቸው ። አዎ እነርሱ ብቻ ናቸው !!

እስራኤል ወረራዋን ፈራ ተባ እያለች ዛሬ ለመግባት እየተንደረደረች ነው ። ሁሉንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ብላለች እስራኤል !

እስራኤል ለማጥፋት ፍልስጤማዊያን ላለመጥፋት የሚያደርጉት ያልተመጣጠነ ትግል በአስከፊው መልኩ ቀጥሏል ።

ነገ ምን እንሰማ ይሆን ? ይህ የሚያስጨንቅ ጥያቄ ነው ።

ይህች አለም ግን የፍርደገምድሎች ሆና ቀጥላለች !

የጋዛ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ከዚች ሰከንድ በኋላ አላህ ከአይሁዶች ጥቃት ይጠብቃችሁ ያረቢ አንተ ድረስላቸው ዱዓ ከማድረግ ዉጪ ምን አቅም አላኝ። በእስራኤል ና በ አንጃዋን አላህ በለዓውን ያውርድባቸው

Send as a message
Share on my page
Share in the group