Mohammed mehdi Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Islam is the best way of life

Translation is not possible.

‏قال الإمام ابن القيم رَحِـمَـهُ الله :

التوحيد : أول ما يدخل به في الإسلام ، وآخر ما يخرج به من الدنيا.كما قال النبي ﷺ : من كان آخر كلامه : لا إله إلا الله ؛ دخل الجنة .فهو أول واجب ، وآخر واجب ، فالتوحيد : أول الأمر وآخره .

- مدارج السالكين(٤١٢/٣) -

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

3. ፍልስጤም በእስልምና ታሪክ ውስጥ

ፍልስጤም ከእስልምና መልእክት ጋር የተላኩ የነቢያቶች ምድር ናት ፡፡ በይቱል መቅዲስ ነቢ ኢብራሂም ፣ ሉጥ ፣ ዳውድ ፣ ሱሌይማን ፣ ሙሳ እና ኢሳ ጨምሮ በርካታ ነቢያት የተወለዱበት ወይም የሞቱበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ ባይቱል-መቅዲስ የመልክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) የኢስራእ እና ሚራጅ ቦታ ነበር፡፡

ፍልስጤም ሁለተኛው የሙስሊሞች ኸሊፋ በሆነው በኡመር ኢብኑ አልኸጣብ ጊዜ በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር ሆነች፡፡ ከዚያም ፍልስጤም የእስላማዊ መንግስት አካል ሆነች፡፡ አዲሱ የእስልምና አገዛዝ በሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል በቤዛንታይን የጭቆና አገዛዝ ስር ይኖሩ በነበሩት የፍልስጤም አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፡፡ የቤዛንታይን ኢምፓየር የአከባቢው ክርስቲያኖችን ከሌላ የክርስቲያን ከፋሎች በመሆናቸው ያሳድድ ነበር፡፡ ሙስሊሞቹ ግን ክፍልፋሎቻቸው ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ክርስቲያኖች የሃይማኖትን ነፃነት አረጋግጠዋል፡፡

በ 1099 AD ፍልስጤም በአውሮፓውያን የመስቀል ጦርኞች ተወረረች በዚህም ምክንያት ለምዕተ ዓመት በነሱ ስር ቆየች፡፡ በወረራው ወቅት ሙስሊሙ ፣ አይሁዳውያኑና የአከባቢው ተወላጅ ክርስቲያን ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋዎች እና ከፍተኛ ግፍ ተፈጽሟል፡፡ በቅዱሱ ምድር ተግባራዊ የሆነው ብቸኛው ሕግ የኃይል እና የስደት ሕግ ነበር ፡፡ የመስቀል ጦረኞች ለ 91 ዓመታት ያህል ሙስሊሞች በቅድስት ምድሯ እንዳያመልኩ ከልክለዋል። አርብ ጥቅምት 2 1187 AD በይተል መቅዲስ በሰላሀዲን አል አዩቢ መሪነት ሙስሊሞች ነፃ አውጥተው ወደ እስላማዊ አገዛዝ መልሰዋል። እናም ጥቅምት 9 1187 ዓርብ ሙስሊሙ ከ 91 ዓመታት ቆይታ በኋላ የመጀመሪያውን ጁመዓ በአል አቅሳ መስጂድ መስገድ ችሏል ፡፡

በ 1917 የእንግሊዝ መንግስት ፍልስጤምን የአይሁዶች ሀገር እንድትሆን ያወጀውን መጥፎ የባልፎር መግለጫ አወጣ፡፡ በዚያን ጊዜ አይሁዶች ከፍልስጤም ህዝብ ውስጥ 8% የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ እናም በግምት 2.5% የሚሆነውን መሬት ይይዛሉ፡፡ በ 1948 ዚዮናውያን በፍልስጤም ምድር ላይ ለራሳቸው መንግስት መመስረታቸውን በመግለጽ እስራኤል ብለው ሰየሟት፡፡ በእንግሊዝ ጦር በተደገፈ ገንዘብ እና መሳሪያ የታጠቀው የዚዮናውያን አሸባሪዎች ወታደራዊ ግፊት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ከፍልስጤም እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ በ 1967 እስራኤል ግብፅን ፣ ዮርዳኖስን እና ሶሪያን በማጥቃት ለመጀመሪያ ጊዜ መስጂድ አል-አቅሳን ጨምሮ ተጨማሪ መሬት ተቆጣጠረች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መስጂድ አል-አቅሳን በእስራኤላውያን የማጥፋት ወይም የማቃጠል የበርካታ ሙከራዎች ዒላማ ሆኖ ቆይቷል፣ ውድቀቱን በድብቅ የመሬት ቁፋሮ ለማምጣት በርካታ ሙከራዎችን ጨምሮ ተደርጓል፡፡ ዚዮናውያን መስጂድ አል-አቅሳ ከእስልምና ሀይማኖት ጋር የለውን ቁሩኝነት ጠንቅቀው ያውቃሉ እናም ማንኛውንም የእስልምና ስልጣኔ ቅሪትን ከመስጂዱ ለማስወገድ ይፈልጋሉ፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group