ለምን ወደ ዋናው ጉዳይ አንመለስም❓ወደ ዲናችን
እኛኮ በጣም ሩቅ የሆነን ነገር እያሰብን ራሳችንን አያደከምን ነው
የሁሉ ነገር መፍትሄው በእጃች ነው።
ትላንትና ሰሃቦችን ጠንካራና የበላይ ያደረጋቸው ነገር ነው ዛሬም እኛን የበላይ ጠንካራ ሊያደርገን የሚችለው።
ሰሃቦች እኮ ከአምልኮ ጀምሮ በሁሉ ነገር ወደር የሌላቸው ሰዎች ነበሩ ። ለእምነታቸው የሚሰጡት ቦታም ከምንም ነገር በላይ ላቅ ያለ ነበር።
በስነ_ ምግባራቸውም ተወዳዳሪ የሌላቸው ምርጥ ትውልድ ነበሩ። ነብዩን በመከተልና ከሀዲያኖችን በመቃረንማ ምኑን አንስተህ ምኑን ትተዋለክ❗️ የተኛውም ቦታ ላይ ይሁኑ ለምን ቤተ መንግስት አይሆንም መተግበር ያለበት የነብዩ ሱና ካለ ከመተግበር ወደ ኋላ አይሉም ። በአላህ ጉዳይ ላይ የማንንም ወቀሳ የሚሰማ ጆሮ የላቸውም። እውነተኞች ነበሩ።
ዒባዳቸው ያማረ ፣ ቸርነታቸው የበዛ ለዱንያ የማይስገበገቡ ፣ እጃቸው ላይ ባለው የሚብቃቁ፣ ከነፍሳቸው ወንድሞቻቸውን የሚያስበልጡ፣ ታዲያ እነዚህ ምርጦቹ የነብዩ ባልደረቦች የበላይነትን ያገኙት ዲናቸውን በማላቃቸው በማክበራቸው ፣በመውደዳቸው እና የአላህን ውዴታ ለማግኘት ጥረት በማድረጋቸው ነው።
እኛስ❓የት ነን❓
ከጠላት ጋር ጂሃዱን እንተወውና
ነፍስያችንን እንታገላት ❗️
ሰላት በመስገድ ላይ ትግል እናድርግ❗️
ውሸትን በመተው ላይ ትግል እናድርግ❗️
የመሳሰሉ ሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንታገል።
በመጀመሪያ ውስጣችን በዒባዳ እናፈርጥም።
ነብዩ ዳውድ عليه السلام
ፆምና ሰላት በጣም ያበዛ ነበር ለዚህም ነበር ጠላትን ሲገናኝ አይሸሽም የተባለው። ምክንያቱም ውስጡ በአምልኮ ደንድኗልና ነው።